Monday, 09 November 2020 00:00

56.2 በመቶ የአለማችን ህዝብ በከተሞች እንደሚኖር ተነገረ

Written by 
Rate this item
(3 votes)


          በአለማችን የከተማ ነዋሪዎች ብዛት በፍጥነት እየጨመረ እንደሚገኝና በአሁኑ ወቅት ከአጠቃላዩ የአለማችን ህዝብ 56.2 በመቶ ያህሉ በከተሞች እንደሚኖር የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ከሰሞኑ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፉት 70 አመታት በአለማቀፍ ደረጃ ያለውን የከተማ ነዋሪዎች ሁኔታ በገመገመበት ጥናት ያወጣውን ሪፖርት ጠቅሶ ፎረሙ በድረገጹ እንዳስነበበው፣ በእነዚህ አመታት በአፍሪካና በእስያ የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር ከእጥፍ በላይ ማደጉን ለማየት ተችሏል፡፡
እ.ኤ.አ እስከ 2050 ድረስ ባሉት አመታት ከአጠቃላዩ የአለም ህዝብ ከ68 በመቶ በላይ የሚሆነው የከተማ ነዋሪ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የጠቆመው መረጃው፣ በ2035 በህዝብ ብዛት ቀዳሚዋ የአለማችን ከተማ ጃካርታ ትሆናለች ተብሎ እንደሚገመትም አመልክቷል፡፡
በመጪዎቹ 50 አመታት ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በሆኑ ከተሞች የሚኖረው ህዝብ ቁጥር አሁን ካለበት 40 ሚሊዮን ወደ 150 ሚሊዮን ከፍ ይላል ተብሎ እንደሚጠበቅም አክሎ ገልጧል፡፡


Read 9082 times