Saturday, 07 November 2020 13:12

ልጅ ማሳደግ ሲባል ምን ማለት ነው?

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 ልጅ እንዲኖራቸው የሚፈልጉ ሁሉ የወላጅነትን ግዴታ እና ኃላፊነት አስቀድመው ተረድ ተው ይሆን የሚለው ጥያቄ healthy place የተሰኘው ድረገጽ ነው፡፡ ወላጅ መሆን የሚ ያስቡ ሰዎች ብዙ በአእምሮ የሚያመላልሱአቸው ነገሮች ለራሳቸው የሚያቀርቡዋቸው ጥያቄ ዎችም አሉ። ለምሳሌም ጡት ማጥባት ትክክል ነውን? ምናልባት ጡት ማጥባት ባልችል ውጤቱ ምን ይሆናል? ሌሊት እንቅልፌን የሚነሳኝ ከሆነ እንዴት እወጣዋለሁ? የመሳሰሉና ሌሎ ችም ጥያቄዎች በቅድሚያ መመለስ ያለባቸው መሆናቸው እርግጥ ነው፡፡ ነገር ግን ሊመለሱ ከሚገባቸው አስፈላጊ ጥያቄዎች ሁለቱ አልተነኩም፡፡ እነርሱም፡- ወላጅነት ምን ማለት ነው? ወላጅ ለመሆን ማሰብ ወይንም መዘጋጀት ምን ማለት ነው? የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህን መረዳት ድርጊትን እንዴት መፈጸም እንደሚቻል፤ የወላጅነትን ግዴታ እንዴት መወጣት እንደሚገባ ትክክለኛውን መረጃ ለማግኘት ይረዳል፡፡ ወላጅ ለሆኑት ወላጆችም አቅጣጫን ይመራል፡፡  
ልጅ ማሳደግ ማለት ምን ማለት ነው?
የተለያዩ አለም አቀፍ መረጃዎች (ዲክሽነሪዎች) እንደሚተነትኑት ከሆነ ልጅ አሳዳጊነት ማለት የሚከተሉት ናቸው፡፡
ልጅን ከተወለደ ጀምሮ እራሱን እስከሚረዳበት ድረስ ማሳደግ፤
ልጅን በማንኛውም ረገድ ብቃት ላለው ደረጃ ማድረስ፤
የወላጅነትን ግዴታ በማሟላት ልጅን በቅርበት በመከታተል ማሳደግ፤
ልጅ ስለተወለደ ብቻ ሳይሆን ልጅ በመሆኑ ብቻ በቅርበት እንደወላጅ ተከታትሎ ማሳደግ፤
ማህበራዊ ደህንነቱ፤ትምህርቱ፤ጤንነቱ፤መኖሪያው፤ምግቡ፤ኢኮኖሚው…ወዘተ የመሳሰሉት ነገሮች ተሟልተው ልጁ አድጎ የራሱን ኑሮ መመስረት እስኪችል ድረስ ማሳደግ በቅርበት መርዳት የመጀመ ሪያው ደረጃ የወላጅ ኃላፊነት ነው፡፡
ከላይ ከተገለጹት የወላጅነት ግዴታ በመነሳት healthy place ድረገጽ የሚያነሳው ተከታይ ጥያቄ….ጥሩ ወላጅ መሆን ሲባል ምን ማለት ነው?የሚል ነው፡፡
ጥሩ ወላጅ መሆን ማለት ልክ ሮቦት እንደተሰኘው መሳሪያ የተሞላውን ወይንም የተሰጠውን ፕሮግራም ብቻ የሚፈጽም አይደለም። ይልቁንም የልጁን ፍላጎት በመከተል እንደፍላጎቱ ድርጊቱን በመለዋወጥ ወይንም በማሻሻል እና አማራጭ መንገዶችን በተሻለ በመፈለግ አስፈ ላጊ ነገሮችን አቅም በፈቀደ በማሟላት ልጅን ማሳደግ ነው፡፡ የአሜሪካው Psychological Association ሶስት ግቦችን ይገልጻል።
ልጅን ጤንቱ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ መንከባከብ፤
ልጆችን ከማንም ተጽእኖ ውጭ እራሳቸውን እንዲረዱ አድርጎ ማሳደግ፤
ልጆች ሊያውቁት የሚገባቸውን እና ከወላጆች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እሴቶች እንዲያውቁ ማድረግ ይገባል፡፡
ስለዚህም ወላጅ መሆን ማለት የልጁን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት፤ ምንም አይነት መጥፎ ነገር እንዳይደርስባቸው መከላከል፤ለወደፊት ህይወታቸው ዝግጁ እንዲሆኑ አድርጎ ማሳደግ፤ፍቅር መስጠት፤በምን መንገድ ማደግ እንዳለባቸው መምራት ማለት ነው፡፡
ወላጅ ግቡ ምን መሆን እንዳለበት አስቀድሞ ማሰብና መዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡ በየቀኑ የሚመለከቱትን ወይም የተለመደውን ነገር ችላ ማለት የተለመደ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን የወለዱትን ልጅ ወይንም እንክብካቤ የሚያደርጉለትን በሚመለከት መዘናጋት ስለማይገባ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለራስ ማንሳት ይገባል፡፡
ልጄ ተባባሪ ወይንስ ለምንም ነገር ፈቃደኛ ያልሆነ ግድየለሽ ልጅ እንዲሆን ነው የምፈልገው?
ልጄ ተስፋ ያለው ወይንስ በቀላሉ ተስፋ የሚቆርጥ እንዲሆን እፈልጋለሁ?
ልጄ በራስ የመተማመን ብቃት ያለው ጠንካራ ሰው መሆን እንዲችል ምን ማድረግ እችላለሁ?
የሚሉትን ጥያቄዎች አስቀድሞ ማንሳት የወላጅነት ግዴታን በተገቢው ለመወጣት ያግዛል።
ወላጆች በጥሩ ሁኔታ ልጆችን አላሳደጉም ሲባል ሊገለጹ የሚችሉ የተወሰኑ ነጥቦችን healthy place ድረገጽ እንደሚከተለው ያስነብባል፡፡
ህጻናት ከወላጆቻቸው ማግኘት የሚገባቸውን ነገር ባለማግኘታቸው ምክንያት ሊበሳጩ እና ሊሰቃዩ ይችላሉ፡፡ መጥፎ በሆነ ደረጃ የተቀመጠ ወላጅ ሲባል ግን አንዳንድ ጊዜ በሚከሰቱ ድንገተኛ አጋጣሚዎች የሚከሰተውን የማያካትት ይሆናል፡፡ መጥፎ የሆነ ወላጅነት ልጆችን ሊጎዳ፤ መጨረሻቸውንም ሊያበላሽ፤ መሆን የሚገባቸውን ነገር ሳይሆኑ እንዲቀሩ ሊያደርግ እንደሚችል መረጃው ይጠቁማል፡፡ ሊደርሱ ይችላሉ ከሚባሉት ጉዳቶች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፡፡
ልጆች እድገታቸው ደካማ እና ወደፊት እድገት የማይታይበት….ጤናቸው የተጎዳ…ሌሎችን የመጉዳት ባህርይ….አመላቸው የተበላሸ መሆን…ወንጀልን የሚፈጽሙ መሆን…ለአጉዋጉል ባህርያት መጋለጥ (መጠጥ፤ ወሲብ፤ ሲጋራ፤ እጽ መጠቀም)….ትምህርት ቤት ደካማ ውጤት የሚያመጡ እና ወደተምህርት ገበታቸውም ለመሄድ አለመፈለግ…እኔ የማደርገው ነገር ትክክል ነው ወይም ለእንዲህ አይነቱ ነገር እኔ የበላይ ነኝ የሚል ስሜት በራሳቸው ላይ ማሳደር…እራስን ማግለል…ማህበራዊ ግንኙነትን መራቅ….ድብርት…እራስን ማግለል… ችግርን ለመቋቋም አለመቻል….ጭንቀት…ፍርሀት…እራስን መጉዳት…በራስ አለመተማ መን…ወዘተ…ናቸው፡፡
ከላይ የተገለጹት ነጥቦች ኃላፊነቱን ባልተወጣ ወላጅ ወይንም መጥፎ ወላጅነት ካላቸው ወላ ጆች የሚገኙ ልጆች የሚያሳዩት ባህርይ ነው እንደመረጃው እማኝነት፡፡ ስለዚህም መጥፎ ወላጅነት የልጆችን የወደፊት ሕይወት ሊያበላሽ የሚችል ድርጊት ይፈጽማል ማለት ይቻ ላል፡፡
በስተመጨረሻ የምናነሳው ጥሩ ወላጅ መሆን ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ይሆናል፡፡
ወላጆች ለልጆቻቸው ሙሉ ድጋፍን የሚያደርጉ ልጆች በሚጠሩዋቸው ቦታ ሁሉ ተገኝተው ወላጅነታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
ወላጆች ልጆቻቸው ሊፈጽሙዋቸው የሚገባቸውን ስነስርአቶች እንዲያውቁና ካልሆነ ምን ጉዳት እንደሚያስከትልባቸው በእርጋታ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ወላጆችና ልጆች መተማመን መቻል አለባቸው፡፡ ወላጆችም ሆኑ ልጆቻቸው እምነትን ጠብቀው ማሳየት አለባቸው፡፡
ጥሩ ወላጅ ማለት በልጆች ጉዳይ በንቃት ተሳታፊ መሆን ማለት ነው፡፡ ልጆች የሚያደርጉዋቸው ነገሮች ቢኖሩ…ወላጆች መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ወላጆች ልጆቻቸው የተስተካከለ አመለካከት እንዲኖራቸው ሊረዱአቸው ይገባል፡፡ ምናልባት ያልተስተካከለ ነገርን ቢረዱ እንኩዋን ወላጆች በጉዳዩ በመግባት አመለካከ ታቸውን ወደቀና አስተሳሰብ መለወጥ ይጠበቅባ ቸዋል፡፡
ወላጆች ለልጆቻቸው እድሜአቸውን ባማከለ መንገድ ሊወጡ የሚገባቸውን ኃላፊነት ሊያስረ ዱዋቸው ይገባል፡፡
ፍቅር መስጠት ወላጆች ለልጆቻቸው ከሚያደርጉዋቸው በጎ ነገሮች ለሁሉም ነገር መነሻ የሚባል ጠንካራ ጎን ነው፡፡ ጥሩ ወላጅነት ፍቅር በመስጠት የሚገለጽ ነው፡፡


Read 13085 times