Sunday, 25 October 2020 00:00

ኢትዮጵያ ከሰሀራ በታች ሀገራት በእድገት በ2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

 አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የዘንድሮ የኢትዮጵያ እድገት በ1.9 በመቶ እንደሚሆን ሲጠቁም፤ መንግስት በበኩሉ፤ 7 በመቶ እድገት ይመዘግባል ብሏል፡፡
አይኤምኤፍ ትናንት ይፋ ባደረገው ከሠሃራ በታች የአፍሪካ ሀገራት የ2020 እና 2021 አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገት ትንበያ መሠረት፤ ካለፈው የፈረንጆች ዓመት አንፃር እድገታቸው ካሽቆለቆሉ ሀገራት ኢትዮጵያ አንዷ ነች ብሏል፡፡ ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገራት የ2020 እድገታቸው ከ0 በታች ኔጌቲቭ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ቤኒን፣ ኮትዲቯር እና ኬንያ ከ1በመቶ በላይ እድገት አስመዝግበዋል ብሏል፡፡
በ2020 ከፍተኛውን እድገት ያስመዘገበችው ቤኒን 2 በመቶ (GDP) እድገት አስመዝግባለች፡፡ ኢትዮጵያ በ1.9 በመቶ እድገት ነው በሁለኛነት ደረጃ ላይ የተቀመጠችው፡፡
እ.ኤ.አ በዚሁ ዓመት 2021 የኢትዮጵያ እድገት 0.0 በመቶ ይወርዳል በሚል የተተነበየ ሲሆን ሌሎች ከ0 በታች እድገት አስመዝግበው የነበሩ ሀገራት እድገት ደግሞ በዚሁ ዓመት በእጅጉ ይነቃቃል ብሏል ሪፖርቱ፡፡
በ2021 ከፍተኛ እድገት ይኖራታል የተባለችው ቦትስዋና ስትሆን ሀገሪቱ በ2020 ኔጌቲቭ 9.6 እድገት ያስመዘገበች ሲሆን በቀጣዩ ዓመት በ8.7 በመቶ ታድጋለች ተብሏል፡፡ ጊኒ ደግሞ በ6.2 በመቶ እድገት በሁለተኛነት ተቀምጣለች፡፡
መንግስት በበኩሉ፤ የዘንድሮ አማካይ እድገት 7 በመቶ መሆኑን አስታውቋል፡፡  

Read 1197 times Last modified on Sunday, 25 October 2020 15:27