Friday, 23 October 2020 14:03

ስቲቭ ዎንደር ከ15 አመታት በኋላ 2 ነጠላ ዜማዎችን ለቀቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 ተወዳጁ የፒያኖ ተጫዋችና ድምጻዊ አሜሪካዊው ስቲቭ ዎንደር የመጨረሻውን ስራውን ካሳተመ ከ15 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ማክሰኞ ሁለት አዳዲስ ነጠላ ዜማዎችን ለአድማጮቹ ማቅረቡን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የ70 አመቱ አንጋፋ ድምጻዊ ስቲቭ ዎንደር ያወጣቸው ሁለት ሙዚቃዎች “ዌር ኢዝ አወር ላቭ ሶንግ” እና “ካንት ፑት ኢት ኢን ዘ ሃንድስ ኦፍ ፌት” የሚል ርዕስ ያላቸው ሲሆን፣ በሪፐብሊክ ሪከርድስ ኩባንያ አሳታሚነት ለአድማጭ መቅረባቸውም ተነግሯል፡፡
ድምጻዊው በኢንተርኔት አማካይነት ስለ ሙዚቃዎቹ በሰጠው መግለጫ፣  ሙዚቃዎቹ አለም ከገባችበት የኮሮና ቫይረስ አስከፊ ዘመን እንዲሁም የእርስ በእርስ ግጭት በቅርቡ ነጻ እንደምትወጣ ያለውን ተስፋ የገለጸባቸው እንደሆኑ የተናገረ ሲሆን፣ ጤንነቱን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄም ከወራት በፊት የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተከናውኖለት በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጧል፡፡
“ዌር ኢዝ አወር ላቭ ሶንግ” የተሰኘውን ሙዚቃ ግጥም መጻፍ የጀመረው ገና የ18 አመት ወጣት ሳለ እንደነበር የተናገረው ድምጻዊው፣ ሃሳቡን ለዘመናት ሲያዳብረው ኖሮ በስተመጨረሻ ለፍጻሜ መብቃቱንም አስታውሷል፡፡


Read 878 times