Monday, 19 October 2020 00:00

ፌደራል ፖሊስ ትጥቅ የማስፈታት ስራ እንደሚሰራ አስታወቀ

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)

 “በዚህ አገር ላይ ሁለት ታጣቂ ኃይል ሊኖር አይችልም፡፡” - ፌደራል ፖሊስ
                     
          ታጣቂ ቡድኖችን ትጥቃቸውን በማስፈታት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲገቡ የማድረጉን ተግባር አጥብቆ እንደሚሰራ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ኢ - መደበኛ የሆኑ አደረጃጀቶችንም የማክሰም ስራ ለማከናወን ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል፡፡
ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 11ኛው የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባዔ ሲጠናቀቅ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፤ ኢ-መደበኛ የሆኑ አደረጃጀቶችን ለማክሰም ከህብረተሰቡ ጋር እንደሚሰራና በአገሪቱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ አደረጃጀት እንዳይኖር ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የግጭት መነሻዎችን ማጥናትና በጥናት የተደገፈ የቅድመ መከላከል ስራዎችን ተግባራዊ ማድረግ ውሳኔ የተላለፈበት ጉዳይ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች ያልተሸፈኑ ቦታዎች ላይ ሚሊሻዎችን በአግባቡ በማደራጀት የተናበበ ስራ በመስራት ችግሮችን መፍታት ይቻላል ብለዋል፡፡
“በዚህ አገር ላይ ሁለት ታጣቂ ኃይል ሊኖር አይችልም” ያሉት ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው፤ ታጣቂ ቡድኖች ትጥቃቸውን ፈተው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሊገቡ ይገባል፤ ለዚህ ደግሞ ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡
የሰራዊቱ የደመወዝ ስኬል ተጠንቶ መጠናቀቁን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፤ የሠራዊቱ አባላት የህክምና፤ የቀለብ፤ የሙያ አበል እንዲሁም የትምህርት እድል እንዲያገኙ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡  

Read 1211 times