Saturday, 10 October 2020 13:11

“ቀለምና ውበት” የግጥም መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በወጣቷ ገጣሚ ሄለን ፋንታሁን የተሰናዳውና “ቀለምና ውበት” የሚል ስያሜ የተሰጠው የግጥም ስብስብ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
ወጣቷ ገጣሚ በግጥሞቿ ህልሞቿን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ የፍልስፍና እይታዎቿንና የፍቅር ጉዳዮችን ለመዳሰስ ሞክራለች፡፡ ከ50 በላይ ግጥሞችን ያካተተው መጽሐፉ፣ የገጣሚዋ የመጀመሪያ ስራ ሲሆን በ82 ገጽ ተቀንብቦ በ99 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
“ድንግልና በኢትዮጵያ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
በደራሲና የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ምሩቋ ፍቅርተ ጌትነት ግዛው የተፃፈውና “ድንግልና በኢትዮጵያ” የተሰኘው መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ ነባሩ ባህላችን የት ነው? የሚል ጥያቄ እያነሳ የሚሞግተው መጽሐፉ፣ በዋናነነት በሀገራችን ድንግልናን የመጠበቅና ከጋብቻ በፊት ወሲብ አለመፈፀም ያለውን የጤና የስነ - ልቦሃና ባህላዊ እሴት የሚተነትን ሆኖ አሁን ላይ ያ ባህላችን እየጠፋ በመሄዱ ወጣቱ ለጤና፣ ለስነ ልቦናና ለስነ ተዋልዶ ጤና ችግር እየተጋለጠ በመሆኑ መፍትሔው ምንድን ነው የሚለው ጉዳይ በአትኩሮት እንዲታሰብበት የሚያመላክት ነው ተብሏል፡፡ የመጽሐፉ አሰናጅ በእዚህ እሳቤ ውስጥ በማደጓና በመኖሯ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረችበት ሰዓት “የሚሊኒየም የመታቀብ አምባሳደር” የተሰኘ ማዕረግ አግኝታም እንደነበር ተገልጿል፡፡ በ86 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ99 ብር እና በ14 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 29442 times