Friday, 09 October 2020 11:08

ከፌስቡክ ገጾች በጨረፍታ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 የለምለም "ላሊበላ"- ብራቮ!
                           (ከአሻግሬ ጌታቸው)


             ለለምለም ሃ/ሚካኤል.... "ላሊበላ"  ነጠላ ዜማ - A+ ሰጥቻለሁ!! ሁሉ ነገር ስርአቱን ጠብቆ የተሰራ የሙዚቃ ክሊፕ ነው።
ግጥም:- ሽጋ ነው! በግጥሙ ማስተላለፍ የተፈለገው ታሪክ ተመችቶኛል። (ከተምኛ ትንሽ ቀባ አድርጎታል)
ዜማ:- ዜማው የልጅቷን ድምጽ ልክ በደንብ የጠበቀ ነው፤ አንተነህ ወራሽ ጎበዝ ልጅ ነው። የልጅቷ አቅምና ድምጽ በደንብ ገብቶታል። ከአበበ መለሰ በኋላ ለድምጻውያን በልካቸው ዜማ የሚሰራ ደራሲ እስከዛሬ አልሰማሁም (አልፎ አልፎ ቢመጡም)፡፡ የቴዲ አፍሮን እዚህ ውስጥ ማካተት አይቻልም፤ ለራሱ ስለሚሰራ።
ከሙዚቃው ቅንብር:-  ለዜማ ተመጣጣኝ የሆነ ለስለስ ያሉ ትራኮች ተጠቅሟል ሚኪ፤ የድምጽ ቅጂ ቁልጭ ያለ ነው። ማስተሪንግ ላይ አበጋዝ ተሳትፏል።
ክሊፕ ዳይሬክቲንግ እና ቦታ መረጣ:- የተዋጣለት ስራ ተሰርቷል።
አሁን ደሞ የእኔ የግል ስሜት፡- ልጅት ቆንጆ ናት፤ ድንቡሽቡሽ ያለች ነገር።
እነዚህን ልጆች ወደ መድረክ ያመጣቸው አብረሃም ወልዴ ምስጋና ይግባውና ለሙዚቃችን ውበት ሆነዋል!!
ለማንኛውም የአመቱ ምርጥ ክሊፕና ዜማ ሽልማት ካለ ይገባታል!! የዘንድሮ ሴት ዘፋኞች ልቅም ያለ ስራ በመስራት ሊመሰገኑ ይገባቸዋል።
ባህል፣ ውበት፣ ስርአት፣ ቁንጅና፣ ዜማና ግጥም አንድ ላይ አስተካክሎ በአግባቡ ማቅረብ መታደል ነው። Bravo ለምለም!!

Read 2964 times