Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 28 July 2012 10:20

ከአቦይ ጋር ጥቂት ቆይታ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የሃሳብ ልዩነት ያለ ነው፡፡ ልዩነቱን መድረክ ላይ አምጥቶ ለማሸነፍ መሞከር ትክክለኛ አካሄድ ነው፡፡

ከዛ ውጪ ሞትን መመኘት ከሰውነት እንዴት እንደራቀ የሚያሳይ የወረደ አመለካከት ነው፡፡

የጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊን ጤንነት አስመልክቶ እርስዎ ለአሜሪካን ድምፅ በሰጡት ቃለምልልስ ጠቅላይ ሚ/ሩ ህክምናቸውን ጨርሰው በቅርቡ በስራቸው ላይ እንደሚገኙ ሲገልፁ አቶ በረከት ስምዖን ደግሞ እረፍት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ የቱን እንመን?

ህዝብ ማወቅ ያለበት አቶ በረከት የሰጡትን መግለጫ ነው፡፡ የእሳቸው መግለጫ ኦፊሻል ነው፡፡

እርስዎ ለአሜሪካን ድምፅ ከሰጡት ጋር እንዴት እናስታርቀው?

የግድ መታረቅ አለበት ወይ? የአቶ በረከትን መግለጫ ውሰዱ፡፡

የሁለታችሁም መግለጫ ቀናቶችን አስቆጥረዋል፡፡ የጠቅላይ ሚ/ሩ የጤና ሁኔታ በአሁኑ ወቅት እንዴት ነው?

አጠገቡ ካሉ ሰዎች እንደምሰማው ጤንነቱ በፍጥነት እየተሻሻለ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚ/ሩ ያሉበትን ቦታ አስመልክቶም የተለያዩ መረጃዎች ይወጣሉ፡፡ የት ነው ያሉት?

አውሮፓ

አውሮፓ የት?

በትክክል አላውቀውም፡፡

ለእረፍት አሜሪካን ሄዱ ተብሏል

አይመስለኝም፡፡

የቀድሞው የህወሓት ታጋይ የነበሩት አቶ ግደይ ዘርአፅዮን “ጠቅላይ ሚ/ሩ ቢሞቱ ለአገሪቱ መፍትሄ ይሆናል” በማለት የሰጡትን አስተያየት እንዴት አዩት?

የሃሳብ ልዩነት ያለ ነው፡፡ ልዩነቱን መድረክ ላይ አምጥቶ ለማሸነፍ መሞከር ትክክለኛ አካሄድ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ሞትን መመኘት ከሰውነት እንዴት እንደራቀ የሚያሳይ የወረደ አመለካከት ነው፡፡

በቅርቡ አድዋ የሚገኘው የንግስተ ሳባ ትምህርት ቤት ሰባኛ ዓመት ሲከበር እርስዎ የደርግ ዘመን የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩትን ኮለኔል ፍስሀ ደስታን ይዘው ሄደው ነበር፡፡ እስቲ ስለሱ ይንገሩኝ፡፡

የንግስተ ሳባ 70ኛ ዓመት የተከበረው ለተከታታይ አራት ቀናት ነበር፡፡ በአሉ በሚከበርበት ወቅት የትምህርት ቤቱን ታሪክ አስመልክቶ የፓናል ውይይት ነበር፡፡

የትምህርት ቤቱ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ሚና ያለው፣ እኔን ጨምሮ ብዙዎችን ጥሩ ተማሪዎች እንድንሆን ያደረገን የፍሰሀ ደስታ ታላቅ ወንድም፣ የት/ቤቱ ዳይሬክተር የነበረው መኮንን ደስታ ነው፡፡ ፍሰሀ ደስታ ደግሞ የቀድሞው የት/ቤቱ ተማሪ ነው፡፡ የኔ የታናሽ ወንድሜ ጓደኛ ነው፡፡

ስለዚህ በዚህ በአል መካፈል አለበት፤ መለየት የለበትም ስል ራሴ ጠይቄው ነው የወሰድኩት፡፡

ፍሰሀ ደስታ የደርግ ምክትል ፕሬዚደንት ነበር፡፡ ፍሰሀ ደስታን መንግስት ሌሎች የደርግ ባለስልጣኖችን ሲፈታ ፈትቶታል፡፡ በቀረው እድሜ ደስ ብሎት እንዲኖር እፈልጋለሁ፤ መገለል የለበትም፡፡ እስር ቤት ሆኖም እጠይቀው ነበር፡፡

አድዋ ስትደርሱ ምን ስሜት ፈጠረ?

የሚበዛው ሰው ተገረመ!! አንዳንዶች ደስ አላቸው!! ቅር ያላቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እኔን በግልፅ ወጥቶ የተናገረኝ የለም፡፡ እኔም ለምን ቅር አላቸው? ለምን ደስ አላቸው ወይም ለምን ገረማቸው ለሚለው መልስ አልሰጥም!! እኔን ደስ ያለኝን ሌላን ሰው የማይጐዳ ነገር አድርጌያለሁ፡፡

የደርግ ባለስልጣን ከነበሩ ሌሎች ጋርስ ቅርበት አለዎት?

በደርግ ጊዜ የግብርና ሚ/ር እና በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከነበረው አሁን በህይወት ከሌለው ከዶ/ር ገረመው ደበሌ ጋር በጣም ወዳጆች ነበርን፡፡ በየቀኑ ነበር የምንገናኘው፡፡

መንግስቱ ግለ መሪ እና ፈላጭ ቆራጭ ነበር፡፡ ሌሎቹ የመንግስቱ ጓደኞች ስልጣን ነበራቸው ብዬ አላምንም፡፡ እነሱ ራሳቸውን የበደሉ ናቸው፡፡ ስርአቱን የሚያምኑበት አይመስለኝም፡፡ መንግስቱ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ያጠፋ ሰው በጥፋቱ መቀጣት አለበት፤ እንደሰው ግን መንግስቱ ቢመጣ ሰላም እለዋለሁ፡፡

እርስዎ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሃሳብዎን ይገልፃሉ፡፡ ለጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ይህ ከየት የመጣ ነው?

ጋዜጦቹ ሲፅፉብኝ የፃፉትን መሰረት አድርጌ መልስ መስጠት መብቴም ግዴታዬም ነው፡፡ ባይፅፉ ኖሮ ጋዜጣ ላይ አልፅፍም፡፡

የአሜሪካን ድምፅም ስለጠየቀኝ ነው የተናገርኩት፡፡ አንቺም ስለጠየቅሽኝ እኮ ነው መልስ የምሰጥሽ፡፡

 

 

Read 7718 times Last modified on Saturday, 28 July 2012 10:25

Latest from