Saturday, 19 September 2020 13:24

በዓመት 600 ሚ. ዶላር ለውጭ ወለድ ተከፍሏል

Written by 
Rate this item
(6 votes)

 የመንግስት የውጭ እዳ ከ28. ቢ. ዶላር በላይ ነው

           በፍጥነት እየገዘፈ የመጣው የመንግስት የውጭ እዳ ባለፉት ሁለት ዓመታት ቢረጋጋም፤ በ2012 ዓ.ም ከ28.6 ቢሊዮን ዶላር ሆኗል፡፡ የውጭ እዳ ለመክፈል የሚውለው ገንዘብ፣ የአገሪቱን መንግስት የሚፈታተን ሸክም ከመሆኑም በተጨማሪ ከዓመት ዓመት እየከበደ መጥቷል፡፡
በ2002 መንግስት ለውጭ እዳ 100 ሚሊዮን ዶላር ከፍሏል፡፡ በ2005 ግን የውጭ እዳ ክፍያው፣ እጥፍ ድርብ ስለጨመረ  ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ አልፏል፡፡ በዚሁ አልተገታም፤ተባባሰ እንጂ አልተቃለለም፡፡ በ2008 ዓ.ም  መንግስት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ለውጭ እዳ ከፍሏል፡፡  የእዳ ክፍያ ጣሪያ የደረሰው ካቻምና ነው፡፡ የዕዳ ክፍያው፣ በ2011 ዓ.ም ከ2 ቢሊዮን ዶላር አልፏል፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ሪፖርት እንደገለጸው፤ የዕዳ ክፍያ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ተረጋግቷል፡፡ መንግስት ለውጭ እዳ 1.99 ቢሊዮን ዶላር ከፍሏል - ለሁለት ቢሊዮን ትንሽ የቀረው፡፡ 600 ሚሊዮን ዶላር የተከፈለው ለብድር ወለድ ነው፡፡ 1.39 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ፣ ዋናውን እዳ ለማቃለል፡፡ አሁን ባለው የብሔራዊ ባንክ ምንዛሬ ከተሰላ ፤የወለድ ክፍያው ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ነው፡፡ በአጠቃላይ የውጭ ዕዳ ክፍያው ደግሞ 70 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው፡፡


Read 5684 times