Wednesday, 16 September 2020 15:52

ሰዎች! እንዴት ነው የማንግባባው!

Written by  (መስፍን ወልደ ማርያም)
Rate this item
(0 votes)

እሰክንድር ባመነበትና በመሰለው ግልጽ አቅዋም ተመርኩዞ፣ ሽንጡን ገትሮ እምነቱን ማሰማቱ አንድ ነገር ነው፤ መስፍን ወልደ ማርያም ስለቤት ማፍረስና ሰዎችን ማፈናቀል የጮኸው ለብቻው አንድ ነገር ነው፤ ኢዜማ ዝርዝር መረጃ ይዞ የገለጠውና ከግምትና ከስሜት ያወጣን ፈጽሞ ሌላ ነገር ነው! እነዚህን ሦስት ነገሮች ለይቶ ማየት ካቃተን በትልቅ የአስተሳሰብ ግርዶሽ ተከፋፍለናል ማለት ነው፤ ግንበ ሰናዖር!
እባካችሁ እናስብ! የመኖሪያ ቤቶችን ማፍረስ የሚያስገኘው ጥቅም ሳይኖር አይቀርም ማለትና የተገኘውን ጥቅም ዘርዝሮ መናገር የተለያዩ ነገሮች ናቸው፤ አንዱን ይዞ ፍርድ ቤት መቆም ይቻላል፤ ሌላውን ይዞ ግን አይቻልም፡፡ ማሰብኮ ቀላል ሥራ አይደለም!
(ነሐሴ 2012)

Read 2798 times