Saturday, 05 September 2020 13:27

ወደ አገሩ የተመለሰ ቅርስ!

Written by  (አሌክስ አብርሃም)
Rate this item
(0 votes)

 ሳፈቅርሽ …
እንደኤሊ በድንጋይ ክንፍ እበራለሁ
እንደፀሐይ በሌሊት፣ እንደጨረቃ በቀን፣ በምድር ላይ አበራለሁ
ሳላስብሽ ያለሽበት እመጣለሁ!
ሳፈቅርሽ
ድመቶች እምቧቧቧ እያሉ መስኩ ላይ ግጦሽ ሲግጡ ላሞች በየጓዳው ውስጥ  ወጥ መድ ፈር ተው ሲሸጎጡ ጭው ያለው ምድረበዳ ላይ ልምላሜውን እያየሁ
አልጋዬ ላይ አደን ውዬ ጫካ ሄጄ እተኛለሁ
ሳላስብሽ በውብ ህልሜ አይሻለሁ!
ዛሬ ግን ...ገና በጧቱ …ነፍሴ ፈራ፣ ተጨነቀ
ልቤ ላይ የከሰመ ፍቅር ጭንቅላቴ ውስጥ ፀደቀ
እናም የማለዳ ፀሃይ በምስራቅ በኩል ዘለቀ!
የሆነ ችግር አለ …ጀመርኩ እንደሰው ማሰብ
ምንድነው ሒሳብ መቀመር፣ ምንድነው ከራስ መሰብሰብ? ይሄው ሳወጣ ሳወርድ ከአልጋዬ ላይ መች ተነሳሁ
በጧት ወዳንች መሮጡን ሳስብኮነው የረሳሁ!
“ሳትክ ተሳሳትክ” ለሚሉኝ ያልገባቸው የፍቅር ሃቅ እውነት ካሉት ታዛ ማደር …እብደት ካሉት ልብ መራቅ !


Read 2875 times