Sunday, 23 August 2020 00:00

ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ክትባት በርካሽ ዋጋ ከሚያገኙት አገራት አንዷ ሆነች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(5 votes)

 ክትባቱ እስከመጪው ጥር ወር ተመርቶ ይከፋፈላል
                  
            ኢትዮጵያ በመጪው ጥር ወር የኮሮና ቫይረስ ክትባትን በርካሽ ዋጋ ከሚያገኙት 92 አገራት መካከል አንዷ ሆና ተመርጣለች::
ክትባቱ ከ3 ዶላር በማይበልጥ ዋጋ ለአገራቱ ይከፋፈላል ተብሏል፡፡
አለማቀፍ የክትባቶች ትብብር (Gavi) ባወጣው መረጃ እንደጠቆመው፤ በመጪው የፈረንጆች ዓመት መግቢያ ላይ እንደሚደርስ የሚጠበቀውን የኮቪድ -19 ክትባት በርካሽ ዋጋ የሚያገኙ 92 አገራት ተመርጠዋል:: አገራቱ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሲሆኑ የዜጐቻቸውን ህይወት ከቫይረሱ ለመታደግ ተነግሯል፡፡
ከእነዚህ አገራት መካከልም ኢትዮጵያ አንዷ ሆና መመረጧን አለማቀፍ የክትባቶች ትብብር (Gavi) አስታውቋል፡፡  (Gavi) ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ደረጃቸውን የጠበቁ 100 ሚሊዮን ክትባቶችን ለማምረት ሴረም ከተባለ የህንድ የክትባቶች አምራች ኩባንያ ጋር ውል የፈፀመ ሲሆን ኩባንያው “ሴረም አስትራዚንክ” እና “ኖቫ ቫክስ” በተባሉ የምርምር ተቋማቱ ክትባቶቹን እንደሚያመርትና ከ3 ዶላር በማይበልጥ ዋጋ ለ92ቱ አገራት እንደሚከፋፈል ተገልጿል፡፡
ለክትባቱ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው የተደረጉትን አገራት ምርጫ የ(Gavi) ቦርድ ማፅደቁንና የክትባት ማምረት ሂደቱ በመጪው የፈረንጆች አመት መግቢያ ላይ ሲጠናቀቅ ለአገራቱ እንደሚከፋፈል ተጠቁሟል፡፡

Read 9139 times