Saturday, 21 July 2012 09:54

ምሬቴ!

Written by  ዶ/ር ፍቃዱ አየለ feke40ayema@gmail.com
Rate this item
(1 Vote)

ያላለቁ «ቤቶች»

ከአንድ በቅር ከተለቀቀ መዘራዝር ችላ የማይባል ..ስሌታዊ ሃቅ.. ቃረምኩና ቅር አለኝ፡

ሰላሳ ብቻ የሚሆኑ ቢሊየነሮች ያግበሰበሱት የሃብት ብዛት የሶስት ቢሊየን ድሆችን የሃብት ድምር ያክላል አ፡፡ለካስ ስፍር ቁጥር የሌለን እኛ ከባለጠጎቹ ያፈተለከችን ቁሪት እየተመነታተፍን ነው የምንኖረው፡፡በዓለማችን ላይ እውነተኛ መተሳሰብ ቢኖር ኖሮ አንዱ ህዝብ በኑሮ ውድነት ጦስ ከየጓዳው ገንፍሎ እየተመመ ያችኑ ያለችውን ቋሚ ሃብት በእሳት እያጋየ በድንጋይ ናዳ ሲያንኮታኩት ሌላው ህዝብ ደግሞ አዳዲስ ..የውሾች ዳንስ ቤት.. ድል ባለ ፌሽታ አስመርቆ ለውሾች ደስታ በተቀመረ ልዩ ዚቃ በአዲስ የውሾች ዓለም ውሾች አለማቸውን ሲቀ ባላሳየን ነበር፡፡

በእንደዚህ አይነት ልዩነት ሰው የሚኖርባት ይህች ዓለም አንዱ እየቆረቆዘ ሌላው በቁንጣን ሆዱን የሚያሽበት ሰበብ በቂ የሆነ የሃብት ምንጭ ስለሌላት አይደለም (ባለቁንጣኑ የቆረቆዘውም አንዱ ለሌላው እንደዚያ መሆን ምክንያት ስለሆኑ ይውደ የሚል ፍርድ አልወጣኝም) ነገር ግን እነዚህ ሁለት የህይወት ጫፎች የሰው ዘር እንዲህ አይነት ልዩነቶችን ለመፍታት የሚያስችል የሞራል ብቃት ለማጣቱ ዋና ማመሳከሪያ ናቸው፡፡ የሰው ዘር ስልጣኔ የላይ የላይ መሆኑን ለመገንዘብ ታላቅ ..አሰላሳይ.. መሆንን አይጠይቅም ፡፡ያለፉት ጥቂት ዓመታትን የኪነ-ክህሎት  (technology) አስገራሚ እመርታ ብቻ በመመልከት ሰው በሳይንስ አማካይነት ግስጋሴውን እያፋፋመ መሆኑን መረዳት ቀላል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ግስጋሴ እንደ ኮሸሌ እሳት ጅር ብሎ ቢነድም ውስጣዊ ማንነትን የሚለውጥ ሆኖ አልተገኘም ፡፡ የድሎትን መጠን ሰማይ ጠቀስ ለማድረግ ገንዘብን አላመው ያደረገው ..ሳይንሳዊ ፍንዳታ.. ቢሊየኖችን ከድህነት ከማውጣት ይልቅ በገንዘባቸው ጉልበት ሳይንሱን እንደ ቦይ ውሃ ወደ ልባቸው መሻት እያጎረፉት ላ ጥቂት ባለጠጎች ..የእርሻ በሬ.. ተደርጎ ሲታረስበት እያየን ነው፡፡ የሰው ዘር  ሳይሰለጥን በፊት ያከናውን የነበረውን ያንኑ እንስሳዊ ትወናውን የስልጣኔ ኮት አጥልቆለት መወናወኑን ቢቀጥልም ግብረገባዊ ባህሪው ግን ከስልጣኔው ጋር አብሮ አልተመነደገም፡፡

የሳይንሱ ዓለም ለመተላለቂያነት ለሚያገለግ ክህሎቶለድሎለቅንጦት እና ለመምነሽነሽ እየተጠቀመ ያለውን የተመራመሪዎችን ጭንቅላት የድህነትን አዋራጅነት ለመዋጋት ተገልግሎበት ቢሆን ኖሮ ይህ ሁ ትርምስ ባልኖረ ነበር፡፡ለመሆኑ የሰው ዘር የገዛ ችግሩን ..ሊጠፋ የሚገባው ችግሬ.. እያለ ከማፋቸል ወጥቶ   ባለ በሌለ ሃይ በተግባር እንዳይረባረብ ያደረገው ነገር ምንድን ነው?

በዚህ የድህረ ስልጣኔ ዘመን ደግሞ በተለየ ፍጥነት እየተደከመበትና እየረቀቀ የሚስገመገመው የኤሌክትሮኒክስና የመረጃ ኪነ-ክህሎት ግስጋሴ ለማስተዋል በሚከብድ ፍጥነት እየተመመ ነው ፡፡ ይህም አብዛኛውን ሰው እንደ ፋብሪካ ውጤት በሁ ነገር ተመሳሳይ እያደረገው ሲሄድ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡ ዘመኑ የክፉ ምስስሎሽ ዘመን ሆኗል፡፡ምስስሎ በበጎነት የሚገለጥ ቢሆን እጅግ መልካም በሆነ ነበ ዳሩ ግን የአብዛኛው የውስ መሻት አንድን የህይወት መጨረሻ ተብሎ የተደመደመን ግብ ለማግኘት ሲሆን እያንድ አንዱ ወዲዚያ ግብ ለመድረስ በሚያደርገው ርብርብ እየተጨፈላለቀ የመጨፍለቅና የመጨፍለቅ ውጤትን በተቀዳጀው መጠን ጨፍላቂውም ተጨፍላቂውም መቋመ እየበረታ ይሄዳል፡፡ሰው ባለጠግነትን ከመጠን ይልቅ የሚቋምጥበት ምክንያት ..እነደነእንትና.. የመሆንን ጥማቱን ለማስታገስ ነው እንጂ ልክነትንና ልክ አልባነትን መዝኖ እየተሆነ ያለው ነገር ..እውነት ወይስ ሃሰት.. ብሎ በመቀመሩ  አይደለም፡፡ከውድቀት ጊዜ ጀምሮ እሰከዛሬ የሰው ልጅ ..እንደ. . ... ለመሆን በመዳከር ላይ ይገኛ ግን ..እንሁነው.. እየተባለ የሚዘፈንለት ያ ግብ በተፈጸመ ጊዜ እጅግ የበዙ ጎስቋላ የኑሮ ተዋናያንን የመቀፍቀፍ ፋይዳ ቢስነቱን ነው ያስኮመኮመን፡፡በእኔ እይታ ጉስቁልና የአፍሪካ ህዝብ ያለውዴታው የሚተውነው ቲያትር ነ ሰው ሊኖረው የማይገባውን ህይወት የኖረ ጊዜ ትወና እንጂ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል፡፡ ለችግ ለችጋር እና ለእርዛት ያልተፈጠረ የሰው ዘር በእነዚህ ክፉ ገጠመኞች ሲለገለግ ውድ ህይወትን  በቁም መነጠቅ ሆኖ ቢያገኘው ልክ ነው ባይ ነኝ፡፡

እስቲ ደግመን አስረግጠን እንጠይቅ፡፡

የችጋ የችግር እና የቸነፈር ድምር ውጤት የሆነው የድህነት ምንጭ ምንድን ነው

(የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ አገር ከአገር ህዝብ ከህዝብ እንዲቆራቆሱ የሚያደርገው የጦርነት መሰረታዊ ሰበብ ምንድን ነው( አንዱ በብርቱ እየጣረ እየለፋና እየደከመ ሳይሞላለት እንደቆዘመ ውሎ አንጀቱ እነደታጠፈ ሲያድረ ሌላው ስላሞጠሞጠ እንዲበለጥግ የሆነበት ምክንያት ምንድን ነው( ባለኦረጂና ተገፍቶ ባለ ፎቶኮፒው የሚሞካሽበት ምክንያቱ ምንድን ነው( ድሃው  የተፈጠረበትን ቀን እየረገመ ባለጠጋው አስር ነፍስን ከእግዚአብሄር ያለ ሃፍረት እንዲለምን የተደረገበት ምክንያቱ ምንድን ነው( ስልጣኔ እንደ ..ሮኬት.. በሚምዘገዘግበት  በዚህ ክፍለ ዘመንም እንኳ ሰው ..እፎይ ስፈልጋት የነበረችው ሰላሜ ተገኘች.. ብሎ እንዳይረካ ያደረገው ያ ነገር ምንድን ነው( ህዝብ ..በቃህ ውረድ.. እያለ ..ውረድ ተባዩ.. ሞቼ ነው ቆሜ ብሎ ደም እንደ ውሃ የሚቸለስበት ምክንያት ምንድን ነው( የሰው ልጅ ታሪክ መሰረታዊ እንቆቅልሽ ፍችው ምንድን ነው?

የሰው ዘር ሰልጥኛለሁኝ ብሎ ለመሰልጠኑ በማስረጃነት የሚደረድራቸው እልፍ አእላፋት ማስረጃዎች ቢኖሩትም በስልጣኔ ይሰለቀጣል ተብሎ የነበረው ..የሰው ዘር ጉስቁልና.. ዛሬም መንጎማለ በትክክል ሊመለስ ያለመቻ እንቆቅልሽ ፍችው የት ነው( የብዙ ..ለዐገኘጠሰ.. (ስነ...ዎች) ጥርቅም አንዱ እየቆዘመ አንዱ እየፈነ አንዱ እያለቀ አንዱ እየፈነደቀ የመኖሩን ..ያን ምስጢር.. ሊፈታ አልቻለም፡፡ የዛሬ አንድ ሺህ አመትም ጦርነት ነበ ዛሬ ብሶበታል፡፡ የዛሬ አንድ ሺህ አመትም ረሃብ ነበረ ዛሬ የሰው ዘር ሰልጥኖ የሚያደርገውን እያሳጣው ቢሆንም ጦርነት አልቀረም፡፡ የዛሬ ሁለት መቶ አመትም ህፃናት በበሽታና በረሃብ ያልቁ ነበር ዛሬም እየረገፉ ይገኛ፡፡ ስልጣኔ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ካልሰጠ ስልጣኔ ይባል እንጂ በውስ አለመሰልጠንን ማቀፉ አያጠያይቅም፡፡ ወይስ መሰልጠን ጥቂቶች ..ኑሮ እንደዚህ ነው(.. ብለው ድሎታቸውን በእየ መገናኛ ብዙሃኑ ሲያስኮመኩምን አፋቸንን ከፍተን እነሱ የሚትን መሆን እየተመኘን በማስመሰል ዘይቤ ራሳችንን አፍረሰን እየገነባን ያላለቁ ቤቶች ሆነን ማለፍ ነው፡፡

እንግዲህ ሰውን ከቢሊየነሩ እሰከ መናጢው ደሃ ድረስ የሚያራኩተው ..ያ ነገር.. በእራሱ በሰው ማንነት ውስጥ ያለ ..ውድቀት.. ነው፡፡ ዋነኛ ችግር የሆነው ..ያ ነገር.. ከእውነት ጋር መፋታቱ ነው፡፡ በምንም ሊዳፈን ያልቻ ስልጣኔምየትምህርት ብዛት የንባብ ብዛትም የስልጣን መአትምየፍልስፍና ጎርፍ የሃይማኖት ጋጋታም ሊያዳፍነው ያልቻለ ..ያ ነገር.. እውነትን ማንጓጠጥ ነው፡፡እውነትን መጥላት ነው፡፡ በሰው ውስጥ ሰው ሁ የሚሻውን ነገር እያገኘ እንዳይኖር ዋናው ምክንያት የሰው እውነተኛ አለመሆን ነው፡፡ ..ያ ነገር.. በእርግጥ እስካልተፈታ ድረስ ትርምስምሱ ይቀጥላል፡፡ሰው የተፈጠረው ለእውነት እና በእውነት ነ ስለዚህ ያለ እውነት ድህነትም ብልጽግናም መልስ ሊሆኑልን አይችም፡፡በለጸግኩኝ የሚለው አልበለጸግኩም በሚለው ሞትና መከራ ላይ ነው ስኬቱ፡፡ ታሪክ እሱን ነው የሚተርከው፡፡

ያለ እውነት መቼም ሰላም የለም፡፡ቁንጣን የወጠረው ውሸታምም ረሃብ የሚጠብሰው ውሸታምም ፍጻሚያቸው ..ለእውሸት አባት.. የተዘጋጀው የጭንቅ ፍጻሜ ነው፡፡

ምንም ይሁን ምን ለሰው ልጆች ጉስቁልና ምንጭ የሆነው ..ያ ነገር.. ዳበረ በተባለው ስልጣኔ እንኳን አለመፈታቱ እውነተኛ ሆኖ መገኘት ለሰው ዘር ስለ ከበደው ነው፡፡ ለ..እውነተኝነት.. የሚከፈል መስዋዕትነት በሳይንስ ከፍታ ላይ ሆኖ ከመፍዋለል ይልቅ ከባድ ነ በስልጣን አናት ሁ ላ በሃገር ሃብትና ንብረት ሁ ላይ እየተንሳፈፉ ያትን ከማድረግም ይልቅ ከባድ ነው፡፡

..ያ ነገር.. ለእውነት ታማኝ ያለመሆን ነገር በየምድሪቱ ያ መሪ ተብዬዎችን ቀፎዎችና ለከንቱ ደስታና በባለጠግነት ለሚገኝ ክብር ሲ የሚዘርፉና የሚገ አድርጓቸዋል፡፡ ነጋዴ እውነትን በአፍጢሟ ተክሎ በእውሸት ላይ በተገነባ ሃብት እየናጠጠ ሰው የማይደርስባቸው መንገዶች በአየር ላይ ይገንልኝ ይላል አርባምስት ሺህ ዶላር ለእለት አዳር  የሚያስከፍል ቅን ሆቴል ገንብቶ ለእፍረተ ቢስነትና  በባህር ዳርቻዎች ሃውልት ያቆማል፡፡

እንግዲህ እንዲህ ከሆነ አለም በዚህ መልኩ ከተሸበበች እውነት እንደ እብድ ውሻ ከየስፍራው ከተሳደደች እውሸት መንገሱ ምን ያስደንቃል( እውነት ባልተከበረችበት አለም የእውሸት ውጤት የሆነው ትርምስና ምስቅልቅል ስልጣኔን ዘር ትንታኔን ፈንግሎ ..እኔ ነኝ ያለ ይግጠመኝ(.. ቢል ምን ይገርማል፡፡ የሃገራችንም የኑሮ ውድነት ጉዳይ ከዚህ አንፃር ነው ሊታይ የሚገባው፡፡

ስናን በታላቅ ምርምር አዳብሮ የሚሞስስ ትንሽዬና ትልልቅዬ ባለስልጣ ለሞሳሽ አስተዳዳሪዎችና ባለስልጣናት ለምርምራቸውና ለምኞታቸው ማስፈጸሚያ የሚሆኑ ግብአቶችን አቅራቢ ..ነጋዴ.. እና ..ኢንቨስተር.. ተብዬዎች ምድርን ጣታቸው ላይ አጥልቀው እንደመኪና ቁልፍ በሚያሽከረክሩበት ሁኔ ሃገርን ሊረከብ ነው የተባለ  ትውልድ ..ኑሮን ተርጉም.. ሲባል ..መጫጫስ.. ናት በሚልበት ሃገ ሰው በላ ሳይሆን ..በእጅ.. ባለበት ልክ ነው ብልጥግናው በሚባልበት ምድር ኑሮ መወደድ ብቻ ሳይሆን ኑሮ እንደዳመራ እሳት ቢንቦገቦግ ምን ይደንቃል( የዚህ ሁ መሰረታዊ ችግር ምንጭ ..እውነት.. ከየቤታችን ጀምሮ እንስከምንሰራበት ስፍራ ድረስ ጠቃሚነቷ በመናቁ ነው፡፡

ግብረገብነት አለመሰልጠን ተደርጎ በመጣጣ ነው፡፡ ከሰው ዘር የሚበዛው ስለጠንኩኝ በሳይንስ አፈተለኩኝ የሚለው ህሊናውን ቋጥኝ በሚያካክል ውሸት አስጨፍልቆ ነው፡፡ ሁም የሚሰራውን ስራ የተከፈለውን መስዋእትነት ከፍሎ እውነትን የእለት ግብሩ ቢያደርግ እና በውሸት የተገኘ ብልጥግና አጸያፊ መሆኑን እያንድአንዱ ቢያምን ህይወት ..የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጪው.. አለመሆኗን እያንድአንዱ ሰው ቢቀበ የተማረው የትምህርቱን ምጥቀት የውስን ሌባነትና ውሸታምነት ለመደበቂያነትና ያልተማረውን ምስኪን በትምህርት በዳበረ ሞጭላፋነት መናጠቁን  ቢያቆ ባለስልጣን ነኝ የሚል ጉልበተኛ ጉልበቱን ..እውሸትን.. ለማቆላመጫነት ሳይሆን እውነትን ለመጠበቂያነት ቢጠቀምበት ያኔ የእውነት ውጤት የሆኑት ሰላምና ብልጥግና አፍርተው በጎመሩ ነበር፡፡

ሆኖም እያንድ አንዱ የሌላውን ሰው እውነተኛነት በሚናፍቅበት ልክ ራሱን ማጤኑን አሌ ብሎ በእውሸት ትቢት የሚወጥር ከሆነ መቼም ቢሆን ሃቀኛና አስተማማኝ እድገት ሊኖር አይችልም፡፡ እንኳን እዚህ አፍሪካ ውስጥ ..ቁንጮ.. ነን ባት ሃገሮችም እውነትና መንፈሳዊው ግብረገብነት በተክፋፉበት ልክ አለን የሚት እንደጉም ተኖ ክው ሲ ሰምተናል ደግሞም እያየን ነው፡፡

ህፃናት ወጣቱ እውነትን የወደዱና ለእውነት የኖሩ ሲገፉና መድረሻ ሲያ እያዩ ሃሰተኛና አፈጮሌ በጮለለና በወነበደበት መጠን ክብር ሲቀዳጅ በከንቱ ደስታና ጮቤ ምድርን ሲቀውጥ እያዩ በሚያድጉበት ሃገር እንዴት ተደርጎ ነው ..ሃቀኛ.. እድገት የሚኖረው ፡፡

ለእውነት መኖር ..ፋሽኑ.. እንዳለፈ ተደርጎ ..ሃሰተኝነት.. በማስረጃ እስካልተረጋገጠ ድረስ ..እውነተኝነትና.. ..ነቄነት.. ተደርጎ በሚታሰብበት ህብረተሰብ ውስጥ ..ሃቀኛ.. ባለስልጣን ሊኖር የሚችለው እንዴት ነው(መቼም ሃቀኛ እና እውነተኛ የህዝብ መሪዎችን ከቻይና አናስመጣ፡፡

ስለዚህ ከዚህ ኑሮ ውድነት ጀርባ ተደጋግሞ የተነገረ የመንግስት ..ችኮነት.. ችግር ቢኖርም በጠቅላላው በህብረተሰባችን ውስጥ ያለው እውነትን የማጣጣል አሳፋሪ አዝማሚያ ካልተቀረፈ ገና ከዚህም የባሰ አስጨናቂ አኗኗር ይጠብቀናል፡፡የመንግስትን ችኮነት የሚያንቦገግ መቅረዝ ምን ህብረተሰ ውስጥ ነው፡፡

ዛሬ ያነሳሳሁት ጉዳይ የእያንድ አንዳችን ፈንታ ነው ፡፡ ከተማሪው እሰከ አስተማሪው ድረ ከገበሬው እሰከ ባለ ፋብሪካው ድረ ከአለቃ እሰከ ተራ ሰራተኛ ድረስ እያንድ አንዱ ለእውነት የሚከፈልን መስዋዕትነት ለመክፈል ካልተዘጋጀ ከሌላው ሰው እውነትን መጠበቁ ፍርደ ገምድልነት ነው፡፡

እያንድአንዱ ግለሰብ ተግባሩን በግብረገብ  የማይከውን ከሆነ እሱ ከሌሎች ያንን ነገር እንዴት ሊጠብቅ ይችላል፡፡ ..እንትን ለእንትን አብረህ አዝግም.. መሆኑ አይቀርም፡፡ ስለዚህ መንግስት ምንም አይነት ይሁ በውስ ያቀፋቸው ሰዎች እነማንም ይሁኑ ለእውሸት ፊት የማያሳይና እውነትን የጥኝ ያለ ህዝብ ከገጠመው በመስመር መግባቱ አይቀርም፡፡ ለእውነት እንተባበ በድህነት መቆራመድ ካልቀረ ለእውነት ወግኖ መደህየት ይሻላል፡፡ ድህነትን በሌብነት በር በገባ አጋጣሚ ለማሸነፍ እየተመኙ ለድህነታችን ምክንያት የሆኑ የእውነት ጠላቶችንና ሌቦችን በልባችን ማሞካሸትና በአስመሳይነት በአፋችን መሳደብ መሰረታዊው ችግራችን ነው፡፡

በእነሱ ቦታ ብንሆን እነሱ የሚያደርጉትን ላለማድረጋችን እርግጠኛ ባልሆነ ስነ-ልቦና የተጠመደን  ሰብእና ገንብተን ባለንበት ሁኔ አባት ያወረሰንን ..ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋልን .. የልባችን ቅኔ ማህሌት ማደረግ ባልተውንበት የባህሪ ህመም ተቀስፈን ስር የሰደደ ብልጥግናን ከየትም አናመጣው፡፡ እንዲህ አድርጌ ምሬቴን ጣራ ድረስ በሚደርስ የጽሁፍ ኸት የማስተጋባው ብዙዎቻችን በኑሮ ውድነት ወፍጮ እየደቀቅን ስለሆነ ነው፡

የዘራናትን እያጨድን ነው ብዬ ስላሰብኩኝም ነው፡፡ እውነትን ..ገፍተን.. በሃሰት የሚገኝ ሃሰተኛ ብልጽግናን በተጨባጭ ምሳሌነት እያስኮመኮምን ያሳደግነው ..ዘር.. ዛሬ አፍርቶ አሽቶ የእጃችንን እየሰጠን ነው፡፡ ባለስልጣን ተብለው የተዋዋትና መላ ቅጣችንን የሚያወት ሰዎች እኮ ከሰማይ እንደዝናብ የዘነ  አይደም፡፡በዚህ ትውልድ መቅረጫ የተቀረጸ ..ሰውዬ.. ወይም ..ሴትዮ.. ናቸው፡፡ ትውልዱ ሰርቶ መበልጸግን አድካሚ ብቻ ሳይሆን ተገቢም እንዳልሆነ ካሰበ እውነትን መድረሻ አሳጥቶ በእውሸት ጥበብ የተካነ ..ሌባ.. ቢሆን ምን ግርም መሰኘት ያስፈልጋል፡፡

ስለዚህ በኑሮ ውድነት እሳት የመለበለ ዋና ምክንያት የሃሰተኝነትና የሆዳምነት መንሰራፋት በእያንዳንዱ የህብረተሰብ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱ ነው፡፡ስለሆነም መፈራት ያለበት ለማየትና ለመታዘብ የጊዜና የቦታ ሁኔታ የማይገድበውን እግዚአብሄርን የነገሮቻችን ሁ  ምክንያት  ብናደርገው ስልጣኔን የነውር መሸፈኛ ሳይሆን የሰው ዘር መጠቀሚያ እናደርገው ነበር፡፡

ለእውነት መቆ ብልጽግና ለሁ እንዲሆንና የሁም አይነት ጉስቁልና መሰረት አንዲናድ ውሸት እንዲዋረድ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሄር ሃገራችንን በእውነተኛ መሪዎችና የተማሩ ሰዎች ይባርክልን እያልኩ የዛሬን ልሰናበት፡፡

 

 

Read 2241 times Last modified on Saturday, 21 July 2012 10:02