Saturday, 08 August 2020 13:04

“ውሃ እሚያጠፋ እሳት” እየመጣ ነው…

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  ከአመታት በፊት ለህትመት ባበቃው “የአመድ ልጅ እሳት” የተሰኘ የመጀመሪያ የግጥሞች ስብስብ መጽሐፉ የሚታወቀው ገጣሚ እምሻው ገብረ ዮሃንስ፣ እነሆ አሁን ደግሞ “ውሃ እሚያጠፋ እሳት” በሚል ርዕስ ሁለተኛ ስራውን ይዞ መጥቷል፡፡
በሌንስ ማተሚያ ቤት አሳታሚነት በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ የሚውለው “ውሃ እሚያጠፋ እሳት” የግጥሞች ስብስብ መጽሐፍ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ 60 ያህል ግጥሞችን ያካተተ ሲሆን፣ በ50 ብር የመሸጫ ዋጋ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በመጽሐፍት መደብሮችና አዟሪዎች ለገበያ እንደሚቀርብ ተነግሯል፡፡
ከመጽሐፉ ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ከፊሉ ጣና ሃይቅን ከእንቦጭ አረም ለማዳን የተጀመሩ ጥረቶችን ለማገዝ እንደሚውል የገለጸው ገጣሚ እምሻው ገብረ ዮሃንስ፣ በቀጣይ “በረከትን ፍለጋ” የሚል ርዕስ ያለው የአጫጭር ልቦለዶች፣ ወጎችና ግጥሞች ስብስብ መጽሐፉን ለአንባብያን ለማብቃት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡
ገጣሚው ስንኝ ሽጦ ከሚያገኘው ሳንቲም ለጣና ለመለገስ በመፍቀዱ እያደነቅን፣ ከዚህ ቀደም ለንባብ ካበቃው “የአመድ ልጅ እሳት” የተሰኘ መጽሐፉ የቆነጠርናቸውን ሶስት ግጥሞቹን እነሆ ለቅምሻ እንበላችሁ!...
  

Read 7842 times