Saturday, 08 August 2020 12:10

የኮሮና ወረርሽኝ የዘመቻ ምርመራ ተጀመረ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 በአንድ ወር ውስጥ 200ሺ ሰዎች ይመረመራሉ

                • በሐምሌ ወር፣ ኮረናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር፣ ከሰኔው ወር ጋር ሲነፃፀር፣ 3 እጥፍ ሆኗል
                   
            የኮሮና ወረርሺኝ በአገራችን የሚገኝበትን ሁኔታ ለማወቅና በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ ውሣኔ ለመስጠት ያስችላል የተባለ የምርመራ ዘመቻ ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በይፋ ተጀምሯል፡፡
ባለፈው ረቡዕ በይፋ የተጀመረው የምርመራ ዘመቻው፤ ወረርሽኙ በማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የስርጭት መጠን ለማወቅና በአዲሱ ዓመት ሊከወኑ በሚገባቸው ተግባራት ላይ ውሣኔ ለመስጠት እንዲሁም ወረርሽኙ በአገሪቱ ያስከተለውን የጉዳት  መጠን ለማወቅ እንደሚያስችል  የጤና ሚኒስትሯ አስታውቀዋል፡፡
ለአንድ ወር በሚቆየውና 200ሺ ሰዎች ይመረመሩበታል በተባለው በዚህ ዘመቻ ላይ ማህበረሰቡ በፍቃደኝነት ተሳትፎ እንዲያደርግና ሁሉም አካላት ለዚህ ተግባር ስኬታማነት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ፣ የጤና ሚኒስቴርና የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም የፊታችን ማክሰኞ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡   
የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት በሚል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፤ በቅርቡ የጊዜ ገደቡ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሊራዘም እንደሚችልም ይጠበቃል፡፡



Read 1134 times