Print this page
Saturday, 01 August 2020 11:36

ታዳጊነት ወይንም ወጣትነት እና እርግዝና

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

  እድሜአቸው ከ15-19 አመት የሆኑ ታዳጊዎች ወይንም ወጣቶችን እርግዝናን ጎጂነት በተመ ለከተ UNICEF እ.ኤ.አ 31 January 2020 ያወጣውን ወደአማርኛ መልሰን ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ለንባብ ብለነዋል፡፡ የታዳጊዎች እርግዝና ለመሆኑ በአገራችን ምን ይመስላል የሚለውን ለግዜው ባናወሳም ነገር ግን አሁንም የልጅነት ጋብቻ የሚፈጸም እና ጋብቻው ካለ ደግሞ እርግዝናው ሊከሰት የሚችል መሆኑን ድሮም ድርጊቱ ከሚፈጸምባቸው አካባቢዎች መረዳት ይቻላል፡፡ ለዚህ ማሳያም የአንዲት እናት ምስክርነት እንደሚከተለው ነው፡፡
‹‹…እኔ እራሴ በልጅነቴ ተድሬ ነገር ግን እርግዝናዬን በሰላም መገላገል ስላልቻልኩ ልጄንም አጥቼ …እኔም በፊስቱላ ታካሚ ሆኜ በዶ/ር ሐምሊን እርዳታ ሰው ለመሆን በቅቻለሁ፡፡ በደረሰብኝ ሕመም የትዳር ጓዴ አስወጥቶ ሲጥለኝ ቤተሰቤ ግን እፍስፍስ አድርጎ ወደአዲስ አበባ አምጥተውኝ ከበሽታዬ ታክሜ ድኛለ ሁ፡፡ ከዚያ በሁዋላም በየሰው ቤት እየተቀጠርኩ ስሰራ በአሰሪዬ ተደፍሬ አንዲት ሴት ልጅ እዛው እናቴ ጋ ገጠር ሄጄ ወልጄ እናትና አባቴ እንዲያሳድጉአት ትቻት መጣሁ፡፡ ልጅቱ እያደገች መጥታ ገና 13 አመትዋን ስታገባድድ በ2011/የካቲት ወር  ለትዳር ተለመነች፡፡ አ..አ..ይ ልጅትዋማ ትማራለች.. አንሰጥም ሲባሉ …እንግዲያውስ ክብር አይወድላችሁም…እንጠልፋታለን ብለው ሄዱ…እኔም በእኔ ይብቃ ብዬ ልጄን ወደአዲስ አበባ አምጥቼ…ይኼው የ7ኛ ክፍል ተማሪ ሆናልኛለች፡፡ ››
ጥሩነሽ ከኮልፌ
ይህ መረጃ ገና የአንድ አመት ድርጊትን የሚያሳየን ነው፡፡ ይህ ማለት እንግዲህ ድርጊቱ በአገራ ችን ገና እንዳልተወገደ ነው፡፡ ዩኒሴፍ ያወጣው አለም አቀፍ መረጃ እንደሚከተለው ነው፡፡
በታዳጊ አገሮች በየአመቱ በግምት 12 ሚሊዮን የሚሆኑ እድሜአቸው ከ15-19 አመት የሚ ሆናቸው ልጃገረዶች እና እድሜአቸው ከ15 አመት በታች የሆኑ 777,000 ታዳጊዎች ልጅን ይወልዳሉ፡፡  
በታዳጊ ሀገራት በየአመቱ እድሜአቸው ከ15-19 አመት በሚሆናቸው ታዳጊዎች ወደ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ያልታቀዱ እርግዝናዎች ይከሰታሉ፡፡ እድሜአቸው ከ15-19 አመት ባሉ ወጣት ሴቶች በእርግዝናና ልጅን በመውለድ ወቅት በሚያጋጥማቸው ውስብስብ የጤና ችግር የሚከሰተው ሞት በሌላ ምክንያት ከሚገጥማቸው ሞት የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፡፡ በየአመቱ ከ15-19 አመት እድሜ ባላቸው ታዳጊ ሴት ልጆች ላይ ወደ 5.6 ሚሊዮን የሚሆኑ የጽንስ መቋረጥ (ውርጃ) የሚከሰት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ 3.9 ሚሊዮን ያህሉ ደህንነቱ ያልተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሞትን፤ህመምን እና እስከ ሕይወት ፍጻሜ የሚቆይ የጤና እውክታን የሚያስከ ትል መሆኑን ምርምሮች ያሳያሉ፡፡
እድሜአቸው ከ10-19 አመት የሚሆኑ ታዳጊዎች እድሜአቸው ከ20-24 ከሚደርሱት በበለጠ በተ ለያዩ ኢንፌክሽኖች …ደም ግፊት በመሳሰሉት ሕመሞች እንዲሁም ምናልባት እርግዝና ውን ቢገላ ገሉትም እንኩዋን ክብደቱን ያላሟላ ወይንም ጊዜውን ሳይጠብቅ የሚወለድ ልጅን መውለድ እና ጨቅላዎቹም ከፍ ያለ የጤና ችግር ሊገጥማቸው ይችላል፡፡ ዩኒሴፍ የችግሩን መጠን ሲያሳይ በመላው በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በየአመቱ 21 ሚሊዮን የሚሆን እድሜ አቸው ከ15-19 አመት የሚደርሱ ልጃገረዶች እርግዝና የሚያጋጥማቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 12 ሚሊዮን ያህሉ ይወልዳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 777,000 ያህሉ እድሜአቸ ውም 15 አመት እንደማይደርስ ነው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በተለይም ታዳጊዎች ወይንም ወጣቶች ላይ የሚታየው ልጅ የመውለድ መጠን ባለፉት 20 አመታት ወደ 11.6% ያህል ዝቅ ያለ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለምሳሌም በምስራቅ ኤሽያ 7.1 ሲሆን በመካከለኛው አፍሪካ 129.5 መሆኑን ባለሙያዎች ያረጋግጣሉ፡፡  የዚህ ልጅ የመውለድ መጠን በአንድ ሀገር ውስጥም ቢሆን ከአንዱ አካባቢ በሌላው ልዩነት የሚያሳይ መሆኑን ለመረዳት የዩኒሴፍ መረጃ ኢትዮጵያን በምሳሌነት ጠቅሶአል፡፡ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ልጅን የመውለድ መጠን በአዲስ አበባ 1.8 ሲሆን በሶማሊ 7.2፤ እንዲሁም እድሜአቸው ከ15-19 የሆኑ ልጃገረዶች በአዲስ አበባ 3% እና 23% በአፋር መሆኑ ለተለያዩ ሀገራትም ሁኔታ ማሳያ ነው:: ስለሆነም የሚነ  ገረው ቁጥር ሙሉ ለሙሉ ገዥ ሳይሆን ማሳያ መሆኑን ነው ዩኒሴፍ የጠ ቆመው፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ የታዳጊዎች የመውለድ መጠን እየቀነሰ ነው ቢባልም ትክክለኛው የወጣቶች እርግዝና መውለድ ግን በአንዳንድ አገራት ያለው እውነታ የሚያሳየው በታዳጊ  እና በአንዳንድ የአለም አገራት እድሜአቸው ከ15-19 አመት ድረስ ያሉ ወጣቶች እርግዝና ቀንሶአል ማለት አይቻልም:: በአመት ከፍተኛው የመውለድ ቁጥር በምስራቅ እስያ (98,153) እና በምእራብ አፍሪካ (70,423) ናቸው፡፡ የታዳጊዎች ወይንም ወጣቶች እርግዝና በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ችግር መሆኑ የተመዘገበ ሲሆን ይህ እውነታ በአደጉት፤በመካከለኛ እና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት የሚታይ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የወጣቶች ወይንም የታዳጊዎች እርግዝና የሚታ የው በድህነት በሚኖሩ፤የትምህርት እድል ባላገኙ፤ የስራ እድል በሌላቸውና በልማድ ተመስር ተው ድርጊቱን በሚፈጽሙት ዘንድ ነው፡፡
ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሌሎች ምክንያቶችም በልጅነት ለሚከሰቱ እርግዝናዎች ምክንያት መሆናቸው በዩኒሴፍ መረጃ ተጠቁሞአል፡፡
በብዙ ሀገራት ታዳጊዎች ወይንም ወጣቶች ትዳር እንዲመሰርቱ እና ልጅ ወልደው እንዲያሳድጉ ጫና መፍጠሩ፤
በመልማት ላይ ባሉ ሀገራት ወደ 39% የሚሆኑት ታዳጊዎች እድሜአቸው 18 አመት ሳይሞ ላቸው እንዲያገቡ እና ልጅ ወልደው እንዲያሳድጉ ከእነዚህ ውስጥም 12% የሚሆኑት 15 አመት ሳይሞላቸው ወደዚህ ኃላፊነት እንዲገቡ መገደዳቸው፤
ታዳጊዎች እርግዝናውን ሊቀበሉት ባይችሉም እንኩዋን ለማቋረጥ የማይወስኑበት ምክንያት ለድርጊቱ የእውቀት ክህሎት ስለሌላቸው እና የት ሊደረግ እንደሚችል ግንዛቤው ስለሌላቸው፤ እንዲሁም ያልተፈለገ እርግዝናን ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ለማቋረጥ የሚያስችለውን አገልግ ሎት የት እንዴት እንደሚገኝ እና ምን ያህል መብት እንዳላቸው የሚያውቁበት መንገድ ስለሌ ላቸው፤
ታዳጊዎቹ ወይንም ወጣቶቹ ከጤና ባለሙያዎች ሊያገኙ የሚገባቸውን ያልተፈለገ እርግዝና አስቀድሞ የመከላከል ዘዴን እውቀት አለማግኘታቸው፤
በገጠር ያሉ ታዳጊዎች ወይንም ወጣቶች ምናልባት መረጃው እንኩዋን ቢኖራቸው አገልግሎቱን ለማግኘት ከአካባቢያቸው ወጣ ለማለት የመጉዋጉዋዣ ችግር፤የገንዘብ እጥረት፤ መከላከ ያው የት እንደሚገኝ አለማወቅ የመሳሰሉት ችግሮች ያውኩዋቸዋል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች በተጨማሪ ታዳጊዎች በእርግጠኝነት ትክክለኛውና ቀጣይነት ያለው መከላከያ ይህ ነው ብሎ መጠቀም እንዲችሉ ቅርብ የሆነ የባለሙያ እርዳታ ያስፈል ጋቸዋል፡፡ ይህ ብዙ ጊዜ ተግባራዊ ባለመደረጉ በታዳጊ አገራት በየአመቱ ቢያንስ ቢያንስ 10/ ሚሊዮን ያህል ያል ተፈለጉ እርግዝናዎች እድሜአቸው ከ15-19 አመት በሚሆኑት ታዳጊዎች ላይ ይከሰታል፡፡ በተጨማሪም ለታዳጊዎች ያልተፈለገ እርግዝና መንስኤ ከሚሆኑት መካከል ወሲባዊ ጥቃትን ሳይጠቅሱ ማለፍ እንደማይቻል የዩኒሴፍ መረጃ ያሳያል፡፡
ስለዚህ ታዳጊዎች ወይንም ወጣቶች እድሜአቸው ከ15-19 ወይንም ከ15 አመት በታች እያሉ ወደትዳር እንዳይገቡ እና ልጅ በማርገዝ የራሳቸውንም ሕይወት ሆነ ያረገዙት ልጅ ሕይወት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ለማድረግ መንግስታት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከፍተኛ ድርሻ አለ ባቸው፡፡
ይህንን ለማስወገድም በብዙ ሀገራት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያለ ሲሆን ለምሳሌም ቺሊ፤ኢትዮጵያ እና ዩናይትድ ኪንግደም ተጠቃሾች ናቸው ይላል የዩኒሴፍ መረጃ፡፡ እነዚህ ሀገራት በጥሩ አመራርና አስተዳደር እንዲሁም እውቀትን ለማስረጽ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ለሌሎች ሀገራትም ምሳሌ የሚሆኑ መሆናቸውን UNICEF እ.ኤ.አ 31 January 2020 ባወጣው መረጃ አስነብቦአል፡፡  

Read 12590 times