Print this page
Saturday, 18 July 2020 16:44

“የዋልድባና የሕወሓት ፍጥጫ መፅሃፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በአባ ገብረኢየሱስ ኪዳነ ማሪያም የተፃፈውና በዋልድባ ታሪክ፣ ገዳሙን አደጋ ላይ እየጣሉ ባሉ መሪዎች፣ የገዳሙን መነኮሳት አልባሳት ለብሰውና ተመሳስለው ስለሚሰልሉ ግለሰቦችና በጠቃላይ በዋልድባ ገደም ላይ ስለተጋረጠው አደጋ የሚተነትነው “የዋልድባና የሕወሓት ፍጥጫ” “የአባቶቼን ርስት አልሰጥም” መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መፅሃፉ በዋናነት የዋልድባን ገዳም ችግር ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማሳወቅ ለዘነጋውም ለማስታወስ ተብሎ የተሰናዳና የገዳሙ የድረሱልኝ ጥሪ የህዝብ ጆሮ እንዲያገኝ ለማሳሰብ መዘጋጀቱን ፀሐፊው አባ ገብረ ኢየሱስ ኪዳነ ማሪያም በመፅሃፉ መግቢያ አሳስበው መፅሃፉን በማንበብ ህዝቡ ታሪኩን ቅርሱንና ማንነቱን ከማወቅ ባለፈ ገዳሙን ከችግር ለመታደግ ይረዳዋል ብለዋል፡፡
በሰሜን ኢትዮጵያ ለክርስትና መስፋፋት መሰረት የሆነውና ብዙ መንፈሳዊያንን ያፈራውን ዋልድባ ገዳምን ታደጉ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በ187 ገፅ የተቀነበበው መፅሃፉ፤ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 20323 times