Print this page
Tuesday, 30 June 2020 05:28

ታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አለፈ

Written by 
Rate this item
(2 votes)


  ታዋቂው የኦሮሚኛ ቋንቋ ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተተኮሰበት ጥይት ሰኞ ማምሻውን ህይወቱ አለፈ። አርቲስቱ ምሽት ላይ በአዲስ አበባ ገላን ኮንዲሚኒየም አካባቢ በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያስታወቀው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ለኢቢሲ እንደተናሩት፥ የከተማዋ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ግድያውን በመፈፀም የተጠረጠሩ የተወሰኑ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
በወንጀሉ ምርመራ ሂደት የደረሰበትን ደረጃ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ነው ያመለከቱት።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በከተማዋ ሰላማዊና የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ያመለከተት ኮሚሽነሩ ህብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
በወጣቱ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ አሰቃቂ ግድያ የተሰማንን ልባዊ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹና
ለመላው አድናቂዎቹ ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን። ነብስ ይማር።

Read 23206 times
Administrator

Latest from Administrator