Saturday, 27 June 2020 13:23

“እኔ ማን ነኝ” የእንቆቅልሽና የሕጻናት ጨዋታ መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በእንቆቅልሽ አይነትና ባህሪያት ዙሪያ የሚያጠነጥነውና በገላውዲዮስ አለልኝ የተጻፈው “እኔ ማነኝ” መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ።
መጽሐፉ እንቆቅልሾቹን በአማርኛና በእንግሊዝኛ አጣምሮ ከመያዙም በላይ የልጆች የጨዋታ አይነቶችን በአማርኛ ከእነ እንግሊዝኛ ፍቺያቸው ይዟል። ለታላቁ የትውልድ መሀንዲስ ለአርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) መታሰቢያ የተደረገው መጽሐፉ በተለይ ለልጆች በርካታ አዝናኝና አስተማሪ ተረቶችን የጨዋታ አይነቶችንና እንቆቅልሾችን ማካተቱም ታውቋል። በ114 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ60 ብር ለገበያ ቀርቧል።

Read 27482 times