Saturday, 30 May 2020 12:00

የመንግሥት ባለሥልጣናት እስከ ሰኔ 30 ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተጠየቁ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

 የመንግሥት አመራሮችና ተሿሚዎች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ያላቸውን የሀብት መጠን እንዲያስመዘግቡ የፌደራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡
ከወረዳ ሃላፊዎች ጀምሮ ጠ/ሚኒስትሩ ድረስ ያሉ ሁሉም የመንግሥት ሹመኞች ከእነ ባለቤታቸው ንብረታቸውን ማስመዝገብ እንዳለባቸው በሕግ መደንገጉን ያስታወሰው ኮሚሽኑ፤ ሁሉም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተሿሚዎች ቀነ ገደቡ ሳይጠናቀቅ ሀብትና ንብረታቸውን እንዲያስመዘግቡ አሳስቧል፡፡
የአዲስ አበባና ድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ተሻሚዎችን ጨምሮ በክልሎች በየደረጃው ያሉ ተሿሚዎች እንዲሁም የመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተሿሚዎች ሀብታቸውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማስመዝገብ እንዳለባቸው ኮሚሽኑ አስገንዝቧል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የባለሥልጣናትን ሀብት መመዝገቡና ለሚጠይቁ ሕጋዊ አካላት የባለሥልጣናትን ሀብት መጠን ለመግለጽ ፈቃደኛ እንደሆነ መግለፁ የሚታወቅ ሲሆን በዚህኛው ምዝገባ አዳዲስ ተሿሚዎች ከእነ ባለቤታቸው ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ይጠበቃል ተብሏል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሀብታቸውን የማያስመዘግቡ ባለሥልጣናት በሕግ እንደሚጠየቁ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

Read 12132 times