በ1985 ዓ.ም ለአንባቢያን ቀርቦ ተወዳጅነት ያገኘው የደራሲ ዘነበ ወላ ‹‹ሕይወት በባህር ውስጥ›› የተሰኘው መጽሐፍ ከሰሞኑ በድጋሚ ታትሞ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
ደራሲው ከ27 አመት በኋላ መጽሐፉን በድጋሚ ለህትመት ያበቃው በበርካታ አንባቢያን ጥያቄ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በአዲሱ የመጽሐፍ ህትመት ውስጥም ሀሳቦችንና መረጃዎችን በድጋሚ አዳብሮ ማቅረቡ ታውቋል፡፡
መጽሐፉ ስለባህር ውስጥ አስደናቂ ተፈጥሮዎች ሳይንሳዊ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ የሚያቀርብ ሲሆን ለአንባቢያን በ80 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡