Saturday, 14 March 2020 11:11

ጥቃት የተፈፀመባቸውን አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰብ መርሃ ግብር ይካሄዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

    በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ጥቃት የተፈፀመባቸውን አብያተ ክርስቲያናትና ምዕመናን ለማቋቋምና ለመደገፍ የሚያስችል መርሃ ግብር ማህበራቱ በጃንሜዳ አዘጋጁ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማህረ ቅዱሳን፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ህብረት፣ ወልዳ ዳንዲ አቦቲ በጋራ ባዘጋጁት ሕዝባዊ ጉባኤ ላይ ከ30 ሺህ ሰው በላይ ይገኛል ተብሎ የሚገመት ሲሆን በዕለቱም በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞችና በውጭ አገራት መሰል ጉባኤዎች ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በደረሱ ጥቃቶች የወደሙ አብያተ ክርስቲያናት ጥቃት የደረሰባቸውን ምዕመናን መልሶ ለማቋቋም ከ6 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ማህበራቱ በጉዳዩ ላይ የተደረገ ጥናት ጠቅሰው አስታውቀዋል፡፡
መጋቢት 27 ቀን 2012 ከቀኑ 7፡ ሰዓት ጀምሮ መርሃ ግብሩ የሚካሄድ ሲሆን በዕለቱም የተለያዩ መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች ይኖራሉ ተብሏል፡፡


Read 745 times