Saturday, 07 March 2020 12:23

አቶ አቢ ሳኖ የንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆኑ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

    በአምባሳደርነት የተሾሙትን የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊናን በመተካት አቶ አቢ ሳኖ የባንኩ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል፡፡
የቀድሞ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና በግምገማ ከባንኩ ፕሬዚዳንትነት መነሳታቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ የዘገበው “ዋዜማ ራዲዮ”፤ ጠቁሟል፡፡
አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቢ ሣኖ ቀደም ብሎም በባንኩ የተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች የሠሩ ሲሆን እስከተሾሙበት ድረስ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን እንዲሁም የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበርን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ መቆየታቸውም ተገልጿል፡፡
የቀድሞ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉም ከሁለት ሣምንት በፊት የቀድሞውን የባንኩን የቦርድ ሰብሳቢ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አስፋውን ተክተው የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውም ታውቋል፡፡  

Read 1165 times