Saturday, 29 February 2020 11:16

የዳዊት ፀጋዬ የግጥም መድበል ለአንባቢያን ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 መገዳደርና አመፃ በሞላቸው ግጥሞቹና ሀሳቦቹ በይበልጥ የሚታወቀው ደራሲና ገጣሚ ዳዊት ፀጋዬ ከሰሞኑ ርዕስ አልባ የግጥሞች መድበሉን ለንባብ አብቅቷል፡፡
47 ግጥሞችን በ55 ገፆች መጽሐፍ ውስጥ ያካተተው ገጣሚው፤ ‹‹ግጥሞች››፣ ‹‹ዝርወ ግጥሞች›› እና ‹‹ሰም እና ወርቅ›› በሚል ሦስት ክፍሎች አቅርቦታል - ግጥሞቹን፡፡
ከነጭ ሽፋኑ ጀምሮ ርዕስ የለሽ በሆኑ ግጥሞቹ አፈንጋጭነቱ ጎልቶ የሚንፀባረቀው ገጣሚው፤ የምድርን መንግሥት ብቻ ሳይሆን የሰማይን መንግሥት (ፈጣሪን) በእጅጉ ሲገዳደርና ሲጠይቅ ይስተዋላል - በግጥሞቹ:: ‹‹ነጩን›› መደብ መድበሉ በ45 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡


Read 1542 times