Saturday, 29 February 2020 11:25

‹‹ኢ-ፋኖስ›› አጋዥ ትምህርት ቪሲዲ ለገበያ ሊቀርብ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   ‹‹ስኮላር - ኢ ፐብልሸር የተሰኘ ድርጅት ለተማሪዎች አጋዥ የሆኑ ትምህርቶችን በዲቪዲ አምርቶ ለተማሪዎች ማቅረብ ሊጀምር ነው፡፡
ድርጅቱ ‹‹ኢ-ፋኖስ›› በተሰኘ የብራንድ ስያሜው አማካኝነት ድጋፍ ሰጪ የትምህርትና የስልጠና ማቴሪያሎችን በመልቲ ሚዲያ መልክ ለማምረትና ለተጠቃሚው በማንኛውም ዲጂታል ሚዲያ ባለበት ሥፍራ ለማዳረስ የተቋቋመ ድርጅት መሆኑንና መንግሥት የአገሪቱን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዓላማ መያዙንም ሀሙስ ከሰዓት በኋላ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ከ7-10ኛ  ክፍል ያሉ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርቶችን፣ ከ11-12ኛ ያሉ የሒሳብና የሳይንስ ትምህርቶችን እንዲሁም ከኬጂ እስከ 6ኛ ክፍል ያሉ የእንግሊዝኛ፣ የአማርኛ ቋንቋ፣ የአካባቢ ሳይንስ ትምህርቶችን፣ ተረቶችንና ጫዋታዎችን በዲቪዲ አምርቶ ለማሰራጨት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ሀላፊዎቹ ባለፈው ሳምንት በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ተቋሙ ይህንን ለመስራት ከትምህርት ሚኒስቴር እውቅናን ያገኘ ሲሆን መነሻውም የአገራችን ሥርዓተ ትምህርት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡
ይህንን ምርት በሲዲ ከመሸጥ ባለፈ በኢንተርኔት ገበያ ላይም ለማከፋፈል እቅድ ያለው ሲሆን በሲዲ የሚታተመው የይለፍ ፈቃድ ለሌለው ለየትኛውም አካል የማይሰራ ተደርጎ ከቆሊያ ሲዲ አምራች ኩባንያ ጋር በትብብር መስራቱም ተገልጿል፡፡ የአንዱ የትምህርት አጋዥ ሲዲ ዋጋ 98 ብር መሆኑም በዕለቱ ተገልጿል፡፡ በሲዲው፣ ትምህርት፣ የጥናት፣ የሁነቶች፣ ምስሎችና እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የማጣቀሻ (ሪፈረንስ) አገልግሎቶችን አጠቃልሎ የያዘ አጋዥነቱ የጎላ ነው የተባለ ሲሆን በስራው ላይ የውጭና የአገር ውስጥ የትምህርት ኤክስፐርቶችና አማካሪዎች ተሳታፈውበታልም ተብሏል፡፡    

Read 11695 times