Saturday, 22 February 2020 10:54

የዳዊት ፅጌ ‹‹የኔ ዜማ›› አልበም ሐሙስ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  ከአንድ ወር በፊት ለአድማጭ የቀረበውና ከፍተኛ ተቀባይነትን ያተረፈው የድምፃዊው ዳዊት ጽጌ ‹‹የኔ ዜማ›› አልበም ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2012 ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ በማሪዮት ሆቴል ተመረቀ፡፡ በምረቃ ሥነ - ሥርዓቱ ላይ ከድምፃዊው እናትና አባት ጀምሮ ታዋቂ ተዋንያንና ሙዚቀኞች ባለሀብቶች፣ በአልበሙ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች የተገኙ ሲሆን፤ ድምፃዊው ከባለአገሩ አይዶል ጀምሮ እስከ አልበሙ ፍፃሜ ድጋፍ ያደረጉለትን ሁሉ አመስግኖ ሸልሟል፡፡ በምሽቱ ኩኩ ሰብስቤ፣ ፍቅር አዲስ ነቃአ ጥበብ፣ ሄለን በርሄና ራሱ ዳዊት ፅጌ በቅላፄ ባንድ ታጅበው ታዳሚውን ሲያዝናኑ አምሽተዋል፡፡

Read 11560 times