Saturday, 22 February 2020 10:04

ቅዱስ ሲኖዶስ ጠ/ሚኒስትሩን በልዩ ሁኔታ አመሰገነ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(6 votes)

    ለጠ/ሚኒስትሩ ልዩ ምስጋና ያቀረበው የቅዱስ ሲኖዶስ ልዩ ጉባኤ በሁለንተናዊ መልኩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥቅምን መብትና ክብርን የሚያስጠብቁ ውሳኔዎችን ማስተላለፉ ታውቋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሶስት ቀናት ስብሰባው በዋናነት በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፈተናዎችና ችግሮች ዙሪያ መምከሩን በመግለጫው አስታውቋል፡፡ በስብሰባው ማጠናቀቂያ ባወጣው ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫውም፤ ሲኖዶሱ በአሁኑ ጊዜ  ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ቤተ ክርስቲያኗ የማምለኪያ ቦታ እንድታገኝ ማድረጋቸው እንዲሁም ወደ መንበረ ሥልጣን ከተጠሩበት ጊዜ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ጉዳያቸው አድርገው እየፈፀሙት ያለ አኩሪ መንፈሳዊ ተግባር ሆኖ ስላገኘው የከበረ ምስጋናውን ማቅረቡን አስገንዝቧል፡፡
በዚህ የምላዕተ ጉባዔው መግለጫ በቅርቡ ማለትም ጥር 24 ቀን ለ25 አጥቢያ 2012 ዓ.ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እና 5 በኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ላይ የተፈፀመውን ግድያ አውግዞ መንግሥት ጭካኔ የተሞላበትን የግፍ እርምጃ የፈፀሙ ወንጀለኛ ላይ ጥብቅ ምርመራ አድርጎ ለሕግ እንዲያቀርብ የደረሰበትን መረጃም ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ቦታው ከነ ሙሉ ክብሩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ እንዲሰጥና ቤተ አምልኮው በድጋሚ እንዲገነባ ቅዱስ ሲኖዶስ ጠይቋል፡፡
በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የተሳሳተና የተዛባ መረጃ በማስተላለፍ ስሟን ለማጥፋት ጥረት እያደረጉ ነው ያላቸውን ሚዲያዎች በተለይም ኦኤምኤን፣ የኢቢኤስ እና የኤል ቲቪ በሕግ እንዲጠየቁለት ለመንግሥት አቤቱታ አቅርቧል::

Read 1311 times