Saturday, 15 February 2020 11:30

ከጥራት ደረጃ በታች የሆነ 19ሺ 770 ጀሪካን የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል ታገደ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

    ከጥራት ደረጃ በታች የሆነ 19ሺ 770 ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል መታገዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት ስድስት ወራት 875,691.42 ሜትሪክ ቶን የገቢ ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥር ለማድረግ አቅዶ፣ በ1,465,177.44 ሜትሪክ ቶን ምርቶች ላይ ቁጥጥር አድርጎል፡፡ የቁጥጥር ስራው የተካሄደው አስገዳጅ የኢትዮጵያ የጥራት ደረጃ የወጣላቸው የገቢ ምርቶች ላይ ሲሆን ፓልም የምግብ ዘይት፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ የአርማታ ብረት፣  ሳሙና፣ ሚስማርና የታሸጉ ምግቦች ይገኙበታል፡፡ ቁጥጥር ከተደረገበት የምግብ ዘይት ውስጥ 19ሺ 770 ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት ከደረጃ በታች ሆኖ በመገኘቱ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ ታግዷል፡፡
በተጨማሪም 700 ካርቶን ሚስማር፣ 28.7 ሜ.ቶ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ 600 ፍሬና 23 ጥቅል የአርማታ ብረት፣ 180 ካርቶን ሳሙና፣ 37 ካርቶን  የታሸጉ  ምግቦች፣ 2113 ሜ.ቶ  ጋልቫናይዝድ ኮይል እንዲሁም 934 ከረጢት ሩዝ  ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከጥራት ደረጃ በታች ሆነው በመገኘታቸው እንዳይገቡ ታግደዋል፡፡            
የጥራት ቁጥጥር መደረጉ ከደረጃ በታች የሆኑ አስገዳጅ ደረጃ ያላቸው ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡና የህብረተሰቡን ጤና፣ ደህንነትና ጥቅም እንዳይጎዱ ያስቻለ መሆኑን የገለጸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዳይሮክቶሬት፤ በቀጣይም መ/ቤቱ፣ ይህን ተግባር ከባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት አጠናከሮ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

Read 2557 times