Print this page
Saturday, 08 February 2020 14:55

የፍቅረኞች ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀው የሙዚቃ ድግስ በኩሪፍቱ ወተር ፓርክ አርብ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶችንና የንግድ ትርዒቶችን በማዘጋጀት የሚታወቀው እንዲሁም የመዝናኛ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን የሚተጋው ‹‹ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር›› ቅዳሜ የሚከበረውን የፍቅረኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀው የሙዚቃ ድግስና የእራት ፕሮግራም የፊታችን አርብ የካቲት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ጀምሮ ቢሾፍቱ በሚገኘው ‹‹ኩሪፍቱ ዎተር ፓርክ›› እንደሚካሄድ ገለፀ፡፡ የጆርካ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታደሰ ታምራት ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፣ በዕለቱ የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራና የፍቅር ሙዚቃ አቀንቃኙ ሚካኤል በላይነህ በዋናነት ታዳሚን የሚያዝናኑ ሲሆን በዕለቱ የሚገኙ ድንገቴ (ሰርፕራይዝ) ድምጻዊያንም እንደሚገኙ አቶ ታደሰ ገልፀው፣ በዕለቱ በዚህ ምሽት ለመታደም ለጥንዶች ከቡፌ እራት ጋር 1800 ብር ለአንድ ሰው ከቡፌ እራት ጋር 1200 ብር የመግቢያ ዋጋ የተተመነለት ሲሆን በዕለቱ 1500 ጥንዶች  እና100 ሲንግሎች በድምሩ 4 ሺህ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡ የመግቢያ ትኬቶቹም በአዲስ አበባ፣ በአዳማና በቢሾፍቱ በሚገኙ የዘመን ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች፣ አራት ኪሎ በሚገኘው ሮሚና ካፌና ሬስቶራንት፣ በቦስተን ዴይ ስፓና በኩሪፍቱ ዎተር ፓርክ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ በዕለቱ ፍቅረኞች የማይረሳ ምሽት እንዲያሳልፉ ለማድረግ ጆርካ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑና ዝግጅቱም እስከ ምሽቱ 5፡00 በድምቀት እንደሚቀጥል የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊው ገልፀዋል፡፡



Read 1042 times