Saturday, 08 February 2020 14:58

‹‹ከመደነጋገር መነጋገር›› መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(9 votes)

በዶ/ር ሳሙኤል ወልዴ የተጻፈውና በመነጋገር አገራዊ፣ ማህበረሰባዊ፣ ቤተሰባዊና ማንኛውንም ችግር መፍታት እንደሚቻል የሚተነትነው ‹‹ከመደነጋገር መነጋገር›› የተሰኘው መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
መጽሐፉ በመነጋገር የማይፈታ ችግር ስላለመኖሩ እየተነተነ፣ መነጋገር ማለት ምን ማለት ነው? ማን ለንግግር ወደ ጠረጴዛ ይምጣ? ሀሳብ የሚገለጥባቸው የንግግር አይነቶች ምን አይነት ናቸው የሚሉ ጥያቄዎችን እያነሳ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማሰናሰል ያብራራል፡፡ በስምንት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ216 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ150 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 11368 times