Saturday, 08 February 2020 14:57

‹‹ደህንነቱ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(7 votes)


              የደራሲ ይስማዕከ ወርቁ አዲስ ስራ የሆነው ‹‹ደህንነቱ›› የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በተቃርኖ የተሞሉ የሰው ልጅ እውነታዎች ከታሪክ እስከ ትርክት፣ ከተቋም እስከ ሥረዓት፣ ከግለሰብ እስከ ቡድን፣ ከርዕዮተ ዓለም እስከ ሃይማኖት፣ ያሉ ከፊት ከኋላ የተደቀኑ የአገር ሳንካዎች፣ ሳይድበሰበሱ ፍርጥርጥ ተደርገው ስለመቅረባቸው፣ ስጋትና ተስፋ፣ ክህደትና በቀል፣ እውነትና ውሸት፣ ትርክትና ታሪክ፣ ልማትና ጥፋት ብቻ ተቃርኖዎች የሚፋጠጡበትና በርካታ የአገር ርዕሰ ጉዳይ የሚዳሰስበት ስለመሆኑ ደራሲው ገጽ 5 ላይ ‹‹ሐተታ›› በሚል ርዕስ ባሰፈረው ማስታወሻ ላይ አብራርቷል፡፡
በ40 ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ238 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡


Read 13078 times