Saturday, 08 February 2020 14:50

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሚካኤል ፓምፒኦ የካቲት 9 2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ይፋ ባደረገው መረጃው፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከየካቲት 6 እስከ 14 በሚያደርጉት በ16 ሀገራት ጉብኝት ጀርመን፣ ሳውዲ አረቢያን፣ አማንን፣ ሴኒጋልን አንጐላንና ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የ3 ቀናት ጉብኝት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ከፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ጋር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏለ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በዋናነት በቀጠናው የፀጥታ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ ሲሆን፤ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ላይም ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ሙሐመት ጋርም ይወያያሉ ተብሏል፡፡  


Read 11438 times