Monday, 03 February 2020 12:06

ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹን በስካይ ላይት ሆቴል ያስመርቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

    ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ኢንቨስተር የክብር ዶክትሬት ዲግሪም ያበረክታል
                   
              ዌስተርን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የትምህርት ዘርፍ ሲያስተምራቸው የቆየውን የድህረ ምረቃና የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚከናወን ስነ - ሥርዓት እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡ ዩኒቨርስቲ ኮሌጁ በተሰማሩበት የኢንቨስትመንት መስክ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገትና ለማህበረሰቡ ብልጽግና የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ኢትዮጵያዊ ኢንቨስተር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ እንደሚሰጥ የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ፕሬዚዳንት አቶ አቤቱ መላኩ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ለዘጠነኛ ጊዜ በMBA ፕሮግራም፣ በመጀመሪያ ዲግሪ ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ በንግድ ስራ አመራር ያስተማራቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡ በምረቃ ሥነ - ሥርዓቱ ላይ ክብርት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የሊንከን ዩኒቨርሲቲ ካሊፎርኒያ ፕሬዚዳንት ሚካሂል ብሮድስኪ (ዶ/ር) የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ አምባሳደር ሚካኤል ሬይነር፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ አሜሪካን አገር ካለው ሊንከን ዩኒቨርሲቲ ጋር ሙሉ የስራ ትብብር ስምምነት በመፈፀም ባለፉት 10 ዓመታት ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ትምህርቱ የሚሰጠው ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ በሚመጡ ከፍተኛ ክህሎትና ተጨባጭ የስራ ልምድ ባላቸው ፕሮፌሰሮችና በመደበኛ ደረጃ በክፍል ውስጥ ነው ተብሏል፡፡
ዌስተርን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመስጠት በሀገሪቱ የከፍተኛ ትምህርት ብቃትና ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ እውቅና የተሰጠው መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አቶ አቤቱ መላኩ ተናግረዋል፡፡



Read 2406 times