Print this page
Saturday, 25 January 2020 12:55

በፕሮፌሰር መስፍን ሕይወትና ሥራ ዙሪያ የተሰራ ዘጋቢ ፊልም ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    ዳማከሴ ፊልምና ኢቨንት ኦርጋናይዘር በእውቁ ምሁር ፕሮፌሰር መስፍን ሕይወትና ሥራ ዙሪያ የሰራውን ዘጋቢ ፊልም ሰኞ ጥር 18 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ በ------ ይመረቃል። ዘጋቢ ፊልሙ፤ ፕሮፌሰሩ ለአገራቸው በሶስቱ መንግስታት ያገዛዝ ዘመን በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና በሰብአዊ መብት ዙሪያ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ የሚተርክ ነው ተብሏል፡፡
ዘጋቢ ፊልሙ የተሰራበት አላማም ለአገሩና ለወገኑ ብዙ የሰራ ሰው በቁሙ መመስገን ስለሚገባውና የእንዲህ አይነት ትልልቅ ሰዎችን በርካታ አስተዋጽኦ ሰንዶ በመያዝ ለመጪው ትውልድ ማስተማሪያነት ለመጠቀም መሆኑን ዳማከሴ ኢቨንስት ገልጿል፡፡ ዳማከሴና ጦቢያ ግጥም በጃዝ  በትብብር በሚያስመርቁት በዚህ ዘጋቢ ፊልም የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣
የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ይታደማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡

Read 21801 times