Saturday, 25 January 2020 12:43

‹‹የባህር ሀይሉ ራስ ወርቅ›› መጽሐፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


             የቀድሞው የባህር ሀይል ባልደረባ በነበሩት ፒቲ ኦፊሰር ራስ ወርቅ መንገሻ ግለ ታሪክና በባህር ሀይል ዙሪያ የሚያጠነጥነው ‹‹የባህር ሀይሉ ራስ ወርቅ›› በሚል ርዕስ በራሳቸው በፒቲ ኦፊሰር ራስ ወርቅ መንገሻ ተጽፎ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ ከቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሕንጻ አለፍ ብሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ አዲሱ ሬር አድሚራል ክንዱ ገዙ፣ የቀድሞው ባህር ሃይል ከፍተኛ መኮንኖችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙም ታውቋል፡፡ መጽሐፉ በዋናነት የፒቲ ኦፊሰሩን የባህር ሀይል ቆይታና ሥራ፣ ስለባህር ሀይል ምንነትና ታሪክ በስፋት የሚዳሰስ ሲሆን በ243 ገጽ ተቀንብቦ በ100 ብርና በ15 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡     

Read 21728 times