Saturday, 25 January 2020 12:26

ሀዲስ አለማየሁ ት/ቤት 400 መጽሐፎች ተለገሰ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በእውቁ ደራሲና መምህር የክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ስም የተሰየመውና በትምህርታቸው የላቀ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎችን እየተቀበለ የሚያስተምረው ‹‹ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት›› 400 ያህል የተለያዩ መጽሐፎችን በስጦታ አገኘ፡፡
መጽሐፉን የለገሱት በቅርቡ ያረፉትና ለረጅም ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና ተመራማሪነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ግዛቸው ሁነኛው እንደሆኑ የስጦታ አስተባባሪው ስንታየሁ ወ/ሚካኤል (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
መጽሐፎቹ ለት/ቤቱና ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን አጋዥ ስለሚሆኑ ትልቅ ስጦታ ነው ሲሉ ዶ/ር ስንታየሁ ገልጸው ት/ቤቱ በቀጣይም በውጤታቸው የላቁ ተማሪዎችን እየተቀበለ እንደሚያስተምርና የራሱን ሕንጻ ለመገንባት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት መረከቡን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Read 680 times