Saturday, 18 January 2020 13:14

‹‹ማንነት›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

  በእውቁ አሜሪካዊ ጸሐፊ ፍራንሲስ ፉኩያማ ‹‹Identity›› በሚል ርዕስ ተጽፎ ዝናን ያተረፈውና በዐቢይ ሀብታሙ ‹‹ማንነት›› በሚል ወደ አማርኛ የተተረጐመው መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መጽሐፉ በዋናነት የጊዜውን የማንነት ፖለቲካ፣ ለእውቅና የሚደረግን ትግል፣ በሀያ አንደኛው  ክፍለ ዘመን ሁለት አስርት ዓመታት የተቀየረውን የአለም ፖለቲካና በርካታ አለም አቀፍ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በስፋት የሚተነትን ነው፡፡ መጽሐፉ በተለይም በሰሜን አፍሪካ ‹‹የፀደይ ስፕሪንግ›› ተብሎ የሚጠራውንና በቱኒዚያ የተጀመረውን ከዚያም ወደ ግብጽ ሊቢያና ሌሎች የአፍሪካ አገራት የተዛመተውን አብዮት ከአገራችን ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ጋር እያሰናሰለ ያብራራል፡፡
በ176 ገጽ ተቀንብቦ በ129 ብር ከ99 ሳንቲም የቀረበው መጽሐፉ “እነሆ” መጽሐፍት መደብር በዋናነት ያካፋፍለዋል፡፡

Read 1175 times