የቀድሞ የወታደራዊ መረጃ ሀላፊ በነበሩት ብ/ጀነራል ታደሰ ተክለ ማርያም የተፃፈውና ከ196 እስከ 1983 ዓ.ም የነበረውን የሰሜኑንና የመሃል አገሩን የኢትዮጵያ የእርስ በእርስ ጦርነቶች የሚያትተው ‹‹የኢትዮጵያ የሰሜኑና የመሀል አገሩ የእርስ በእርስ ጦርነቶች›› የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
ፀሐፊው በመጽሐፋቸው ለጦርነቱ መነሻ የነበሩ ምክንያቶችን በየትና እንዴት እንደተካሄዱ በጦርነቱ መሃል ስለተከሰቱ ነገሮች ካዩት ካነበቡት ከኖሩት እያጋመዱ በስፋት ተንትነዋል በሰባት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ343 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ250 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡