Print this page
Sunday, 05 January 2020 00:00

‹‹ዳጉ›› አዲስ አልበም ለአድማጭ ሊቀርብ ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 መኖሪያውን አሜሪካ ሲያትል ያደረገው ድምጻዊ ፀጋ ሙጬ ‹‹ዳጉ›› አዲስ አልበም ሰሞኑን ለአድማጭ ሊቀርብ ነው፡፡ ድምፃዊው ትላንት በኢትዮጵያ ሆቴል በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው 14 ዘፈኖችን ባካተተው አልበሙ ኢትዮጵያዊነትን፣ ፍቅርን፣ ተፈጥሮንና መተሳሰብን ለመግለጽ መሞከሩን ተናግሯል፡፡
አብዛኛውን ግጥምና ዜማ ራሱ ድምጻዊው እንደሰራው ገልጾ 3ቱን ስራዎቹን ጊልዶ ካሳ፣ ቀሪዎቹን የግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ እንዳቀናበረለት ገልጿል፡፡
አልበሙ በአገር ውስጥ እንደሚከፋፈልና ለኦንላይን ገበያ እንደሚቀርብ የተገለፀ ሲሆን ድምፃዊው ከአልበሙ በፊት ለሰራቸው ስድስት የሙዚቃ ቪዲዮዎችና ለአልበሙ በአጠቃላይ 52 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረጉም ታውቋል፡፡

Read 904 times