Saturday, 28 December 2019 14:30

“የጋዜጠኞች ወግ” መጽሐፍ ሐሙስ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  በወጣቱ ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ የተሰናዳውና የአንጋፋ ጋዜጠኞችን ህይወት ከስቱዲዮ እስከ ጦር ሜዳ የሚዘክረው “የጋዜጠኞች ወግ መጽሐፍ የፊታችን ሐሙስ ታህሳስ 23 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በራስ ሆቴል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በዕለቱ ከወጣት እስከ አንጋፋ ጋዜጠኞች በአንድ አዳራሽ ተገናኝተው ልምድ የሚለዋወጡበት፣ አንዱ ጋዜጠኛ የሌላውን ታሪክ መድረክ ላይ ወጥቶ የሚያነብበት፣ አንጋፋ ጋዜጠኞች ከስቱዲዮ እስከ ጦር ሜዳ ያሳለፉትን አሳዛኝ አስቂኝና አስገራሚ ገጠመኝ ለታዳሚ የሚያካፍሉበት፣ የመጽሐፍ ዳሰሳ፣ ግጥምና ሌሎች ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡበት መርሀ ግብር መሰናዳቱንም ጋዜጠኛው ገልጿል፡፡
መጽሐፉ በ180 ገጽ ተቀንብቦ በ100 ብር ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን፤ መታሰቢያነቱም ለሙያው ራሳቸውን ሰጥተው ለኖሩ ጋዜጠኞ ሆኗል፡፡ የዚህ መጽሐፍ ደራሲና ጋዜጠኛ ግዛቸው አሻግሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የመዝናኛ ክፍል፣ በብስራት ሬዲዮ የማራኪ ሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኖ የሰራ ሲሆን በአሁን ወቅት በዋልታ ቴሌቪዥን የማራኪ መዝናኛ አዘጋጅ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

Read 10946 times