Monday, 23 December 2019 00:00

“ዳኝነት ከጥንት እስከ ዛሬ” መጽሐፍ የፊታችን አርብ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   በደራሲ ግርማስላሴ አርአያ የተፃፈውና በኢትዮጵያ ዳኝነት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ‹‹ዳኝነት ከጥንት እስከ ዛሬ›› የተሰኘው መጽሐፍ የፊታችን አርብ ታህሳስ 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በራስ ሆቴል አዳራሽ ይመረቃል፡፡ በዕለቱ የፍልስፍና ምሁሩ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) ደራሲና የሕግ ባለሙያ ውብሸት ሙላት፣ በጎሰው የሸዋስ (ዶ/ር)ና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩ አቶ ተሻገር አስማረ በመጽሐፉ ዙሪያና በአገራችን ሕግና የዳኝነት ታሪክ ላይ የሚያተኩሩ ጽሑፎችን የሚያቀርገቡ ሲሆን በተጨማሪም አጭር ተውኔት፣ ግጥም፣ ወግና ሌሎች ኪነ ጥበባዊ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
የመጽሐፉ ደራሲ ግርማ ስላሴ አርአያ ከ1962 – 1984 ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኝነት እስከ ፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ እና በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤቶቻቸውም በተለያዩ ጆርናሎች ላይ የታተሙላቸው ሲሆን ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ‹‹ሚዛን›› የተሰኘ በሕግ ላይ የሚያተኩር መጽሔት አሳታሚና አዘጋጅ ሆነው ማገልገላቸው አይዘነጋም፡፡

Read 8258 times