Saturday, 30 November 2019 13:11

‹‹የኢትዮጵያ አንድነትና ተግዳሮቶች›› መጽሐፍ በጎንደር ቋራ ሆቴል ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 የአንጋፋው ደራሲ ተክሌ ተሾመ መኮንን አራተኛ ሥራ የሆነውና በወቅቱ የአገራችን ፖለቲካ፣ በአገሪቱና በሕዝቡ ፈተናዎችና በአገር አንድነት ላይ በተጋረጠው ተግዳሮት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ‹‹የኢትዮጵያ አንድነትና ተግዳሮቶች›› መጽሐፍ ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ ጎንደር ከተማ በሚገኘው ቋራ ሆቴል ይመረቃል። በሥነስርዓቱ ላይ ጋዜጠኛና የቴአትር ባለሙያው ዋሴ ነጋሽ በመጽሐፉ ላይ ጥልቅ ዳሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን ውይይትም ይካሄዳል ተብሏል፡፡ መጽሐፉ በ512 ገፆች ተቀንብቦ፣ በ180 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ደራሲው ከዚህ ቀደም ‹‹የደም ዘመን ክፍል 1 እና 2›› እና “የቁልቁለት ጉዞ” የተሰኙ መጽሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፣ በዚህ የምረቃ ሥነስርዓት ላይ አዲስ የተሾሙትን ወጣት ከንቲባ ማስተዋል ስዩምን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ምሁራንና ፖለቲከኞች እንደሚታደሙም የምርቃቱ አዘጋጅ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ጎንደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

Read 9133 times