Saturday, 30 November 2019 13:10

የትንሳኤ ኪነ ጥበብ 3ኛው ምሽት አርብ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   በሳሚ ማስታወቂያና ፕሮሞሽን አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው ‹‹ትንሳኤ የኪነ ጥበብ ምሽት›› ሶስተኛው ወር መሰናዶ የፊታችን አርብ ህዳር 26 ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሳሬም ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሄዳል። በዕለቱም ገጣሚያኑ አስታውሰኝ ረጋሳ፣ ዲበኩሉ ጌታ፣ ሞገስ ወ/ዮሐንስ፣ ሰናይት ጥፍጡ፣ መላኩ ሳህለማርያም፣ ሄለን ፋንታሁን፣ ማርታ ተስፋዬና ሳባ መኩሪያ ግጥም የሚያቀርቡ ሲሆን አርቲስት የትናየት ይልማ ክራር ትጫወታለች ተብሏል፡፡
በኪነት ጥበብ ምሽቱ ዝነኛ ባለሙያዎች ሰዎች ለስኬት ያበቋቸውን ሰዎች የሚያመሰግኑበትና የሚሸልሙበት ሥነስርዓት እንደተዘጋጀም ተገልጿል፡፡ ኮሜዲያን አሰፋ ተገኝና ሌሎችም የኮሜዲ ሥራ የሚያቀርቡ ሲሆን መርሃግብሩ በአፍሪካ የሙዚቃ ባንድ እንደሚታጀብና የመግቢያ ዋጋው 100 ብር እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

Read 9219 times