Saturday, 09 November 2019 11:29

5ኛው የ”ሶርሲንግ” እና የፋሽን ሳምንት ኤክስፖ ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

5ኛው የስራ ማስተላለፍ “ሰርሲንግ” እና የፋሽን ሳምንት ኤክስፖ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ይከፊታል፡፡ በኤክስፖው ላይ የጥጥ፣ የአልባሳት፣ የቆዳ፣ የቴክኖሎጂ፣ የቤት ማስጌጥ (ዲኮር) ጠቅላላ ሽያጭ፣ የቡቲክና የመስተንግዶ (ሆስፒታሊቲ) ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡ በዚህ ኤክስፖ ከ25 አገራት የተውጣጡ ከ280 በላይ ተሳታፊዎች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያርቡ ሲሆን፤ የዘንድሮው ኤግዚቢሽን አምና ከተካሄደው ተመሳሳይ ኤግዚቢሽን የ20 በመቶ ተሳታፊና የ20 በመቶ ጐብኚ ብልጫ ይኖረዋል ተብሎ እንደሚገመት የኤግዚቢሽኑ አስተባባሪ ኢትኤል ኮሚዩኒኬሽን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ማክሰኞ ረፋድ ላይ በራማዳ ሆቴል በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የዘንድሮው የ”ሶርሲንግ” እና የፋሽን ሳምንት ኤግዚቢሽን ከምስራቅ አፍሪካ ከሚመጡ አምራቾች በተጨማሪም ከመላው አፍሪካ የሚመጡትን እንደሚያካትትና ለመጀመሪያ ጊዜ ከጀርመን፣ ከፖርቱጋልና ከፈረንሳይ የዘርፉ ባለሙያዎች የምርት ውጤቶችን ይዘው በመምጣት የሚሳተፉ ሲሆን ኩባንያዎች የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ዕድል እንደሚመቻች ተገልጺል፡፡
ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ከምዕራብና ከምስራቅ አፍሪካ የሚመጡ 20 እውቅ ዲዛይነሮችን ከአለም አቀፍ ገዢዎችና ከብራንድ ፋሸን አምራቾች ጋር በትብብር ለመስራት ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡

Read 7592 times