Saturday, 16 June 2012 12:54

“ሜድ ኢን ቻይና” ነገና ሰኞ ይመረቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በመስፍን ኃይለኢየሱስ (ጠጆ) እና ቴዎድሮስ ስዩም ተፅፎ የተዘጋጀው “ሜድ ኢን ቻይና” ልብ አንጠልጣይ አስቂኝ ፊልም ነገና ሰኞ ይመረቃል፡፡ በአዲስ አበባ እና በክልል በሚገኙ የግል ሲኒማ ቤቶች የሚመረቀው ፊልምን ለመሥራት ከአንድ አመት በላይ የፈጀ ሲሆን የ100 ደቂቃ ርዝመት እንዳለው አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ከሀገር ለመውጣት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን እና ወደ ሀገሩ መመለስ የሚፈልግ ቻይናዊ የሚገጥማቸውን ውጣ ውረድ የሚያሳየውን ፊልም ከአዘጋጆቹ ጋር በመሆን ፕሮዲዩስ ያደረጉት አቶ ዳንኤል ሳህሉ ናቸው፡፡ በፊልሙ ሁለቱን አዘጋጆች ጨምሮ መኮንን ላዕከ፣ ማህደር አሰፋ፣ ይሄነህ ጌታሁን (ከፋራ) እና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

 

 

Read 1047 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 12:57