Saturday, 16 June 2012 12:54

ዮአሰ ጥበብ” ዘመናዊ ፋብሪካውን ዛሬ ያስመርቃል

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

በሀገር ውስጥ እና በውጪ ሀገራት ለገበያ የሚቀርቡ ባህላዊ አልባሳትን በዘመናዊነት የሚያመርት ፋብሪካ ማቋቋሙን “ዮአስ ጥበብ” አስታወቀ፡፡ ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጥቃቅን እና አነስተኛ ምርቶች ማምረቻና መሸጫ ቀበሌ 04 የሚመረቀውን ፋብሪካ በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት ዲዛይነር ሽታዬ ክንፈ ናቸው፡፡ የሽመና ክፍሉ ለ33 የድርጅቱ ሸማኔዎችና ለ42 ከፋብሪካው ውጪ ላሉ ሰዎች የሥራ እድል ያስገኘ ሲሆን በቀን 25 ኪሎ ግራም የሚያመርተው የማቅለሚያ ክፍል ለ5 ሰዎች፣ በወር 600 ልብስ የሚያመርተው የስፌት እና ጥልፍ ክፍሉ ለ10 የድርጅቱ እና ለ15 የውጭ ሰዎች የሥራ እድል አስገኝቷል፡፡

 

 

Read 880 times Last modified on Saturday, 16 June 2012 12:57