• ሙዚቃ የመላዕክት ቋንቋ ነው መባሉ ሲያንስበት ነው፡፡
ቶማስ ካርሊሌ
• ሙዚቃ የፈውስ ሃይል አለው፡፡ ሰዎችን ለጥቂት ሰዓታት ከራሳቸው ውስጥ መንጥቆ የማውጣት አቅም ተችሮታል፡፡
ኢልቶን ጆን
• የምታደምጠውን ሙዚቃ ንገረኝና፣ ማንነትህን እነግርሃለሁ፡፡
ቲፋኒ ዲባርቶሎ
• ሕይወቴን የምመለከተው ከሙዚቃ አንፃር ነው፡፡
አልበርት አንስታይን
• ሙዚቀኞች ጡረታ አይወጡም፤ ሙዚቃ ከውስጣቸው ሲደርቅ ያቆማሉ እንጂ፡፡
ሉዊስ አርምስትሮንግ
• ሙዚቃ የተፈጠረው የሰውን ልጅን ብቸኝነት ለማረጋገጥ ነው፡፡
ሎውረንስ ዱሬል
• አንዳንድ ሰዎች ኑሮ አላቸው፤ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሙዚቃ፡፡
ጆን ግሪን
• ፈጣሪ አያድርገውና ከሞትኩ፣ መቃብሬ ላይ እንዲህ ተብሎ ይፃፍልኝ፡- ‹‹እግዚአብሔር ለመኖሩ የሚፈልገው ብቸኛ ማረጋገጫ ሙዚቃ ነበር››
ኩርት ቮኔገት
• ሙዚቃ በቃላት የማይነገረውንና በዝምታ ሊታለፍ የማይችለውን ይገልጻል፡፡
ቪክቶር ሁጎ
• ብቸኛው የዓለማችን እውነት ሙዚቃ ነው፡፡
ጃክ ኬሮዋክ
• የሙዚቃን ፍሰት ማስቆም ማለት ጊዜን ራሱን እንደ ማስቆም ነው፤ ሊሆንና ሊታሰብ አይችልም፡፡
አሮን ኮፕላንድ
• ‹ሁሉንም ዓይነት ሙዚቃ› እንወዳለን የሚሉ ሰዎች ታውቃላችሁ? እነሱ ምንም ዓይነት ሙዚቃ የማይወዱ ናቸው፡፡
ቹክ ክሎስተ
Published in
ጥበብ