Tuesday, 08 October 2019 09:26

የእናቶችና ሕጻናት ጤና አገልግሎት በብቃትና በጥራት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ESOG የእናቶችና ሕጻናትን ጤናን በተሻለ መንገድ ለመጠበቅና ለመንከባከብ እንዲያስችል ለጤና ተቋማቱ ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርግ የሶስት ወር ፕሮጀክት ነድፎ ወደስራው ተገብቶ ነበር ፡፡ በተለይም በኦሮሚያ በተመረጡ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ተጀ ምሮ የነበረው ሙያተኞችን የማማከርና ልምድ የማካፈል አገልግሎት የሶስት ወር ሂደቱን በማጠናቀቁ የነበረውን አሰራር ለመመልከት የሚያስችል ስብ ሰባ ከምእራብ ሸዋ ዞን (አምቦ ሪፈራል ሆስፒታል) እና ከአርሲ ዞን (አሰላ ሪፈራል ሆስፒታል) ከመጡ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያዎች እና ፕሮግራሙ ተግባራዊ ከተደረገባቸው ሆስፒታሎች እንዲሁም ከክልል እና ከዞን ከመጡ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ጋር ስብሰባው ተካሂዶአል፡፡ ይህ ፕሮጀክት የእናቶችና የህጻናትን ጤንነት አገልግሎት በሚመለከት ጥራትና ብቃት ባለው መንገድ እንዲ ሰራ ለማስቻል የታቀደ ሲሆን ሙያተኞችን የማማከር አንዱ ከሌላው ልምድ እንዲቀስም የማድረግ እንዲሁም የጎደሉ ነገሮች እንዴት እንደሚሟሉ ማሳየትከፕሮግራሞች አላማዎች መካከል የሚጠቀስ ነው፡፡ የጤና ተቋማቱ የእና ቶችንና ጨቅላዎቻቸውን ደህንነት በማረጋገጥ በኩል በተመሳሳይ መልኩ የሚጠቀሙበት ሞዴል እንዲኖር በማድረግ የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ከጤና ጥበቃ ሚኒ ስቴር ጋር በመተባበር ለሶስት ወር ተግባራዊ ያደረገውን ፕሮግራም አፈጻጸም የሆስፒታሎቹን ሪፖርት ለማዳመጥ የተጠራ ስብሰባ ነው ዶ/ር ማለደ ቢራራ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔ ሻሊስት ESOGን በመወከል በስብሰባው ላይ እንደተናገሩት፡፡
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የእናቶችና ህጻናት ጤና ዳይሬክቶሬት የእናቶች፤ አፍላ ወጣቶችና የወጣቶች ኦፊሰር አቶ ሸለመ ሁምኔሳ እንደገለጹት የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይህንን እገዛ እንዲደረግ ፕሮግራም የነደፈ ሲሆን የዚህ ምክንያት ደግሞ፡
ከዩኒቨርሲቲዎቹ ተመርቀው የሚወጡት ባለሙያዎች በቂ እውቀትና ክህሎት ይዘው እንደማይወጡ ለማየት የተቻለ ስለሆነ፤
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ተከታታይነት ያለው የባለሙያዎች እውቀት ማደርጀት አካል ስለሆነ ነው፡፡ አንድ ባለሙያ ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀ በሁዋላ በየጊዜው እራሱን በእውቀት ካላሻሻለ ወይንም በየጊዜው ከሚኖረው የህክምና ሙያ እድገት ጋር እራሱን ብቁ ካላደረገ ከዩኒቨርሲቲ መመረቁ ብቻውን ሙሉ አያደርገውም፡፡
የኢፊድሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዚህ በሶስት ወር ፕሮጀክትም ሆነ በሌሎች ፕሮግራሞች የሚሰጠውን የ Mentor-ship ፕሮግራም እንደ አንድ የሙያ ማበልጸጊያ እና የተገልጋዮችንም ጤንነት በተሟላና ብቃት ባለው የህክምና አገልግሎት መጠበቅ መሆኑን ስለሚያምን በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ ይሰጣል፡፡ በእርግጥ ይህ ባለሙያዎችን በስልጠናና በምክር አገልግሎት የማገዝ ተግባር በቅዱስ ፓውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅና አብሮአቸው ከሚሰራቸው የጤና ተቋማት መካከል የነበረው እንዲሁም በሌሎች ሆስፒታሎችም የሚሰራበትን በተጨማሪም ኤች አይቪ ኤይድስን ከመከላከል አንጻር የተሰሩ ስራዎችን በመመልከት ሲሰራበት የነበረውን የ Mentor-ship ፕሮግራም እንደምሳሌ በመውሰድ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሂደቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም የሚደረግበት ምክንያት በጤና ተቋማት የባለሙያን እውቀት ለማሻሻል እንደ አንድ አቅጣጫ ስለሚያገለግል ነው፡፡
የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት ምክንያት ከሚባሉት መካከል በሶስተኛነት ደረጃ የተቀመጠው በሕክምና ተቋማቱ የሚኖረው መዘግየት ወይንም የህክምና አገልግሎት በተሟላ እውቀትና አደ ረጃጀት አለመሰጠቱ ሲሆን ይህንን ለማሟላት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እገዛ በመደረግ ላይ መሆኑን እና የተለያዩ መመሪያዎች ወደ ባለሙያው አንዲደርስ መደረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ሸለመ ሁምኔሳ ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌም አሉ አቶ ሸለመ… ለምሳሌም እናቶች ከወለዱ በሁዋላ 24 ሰአት ማቆየት የሚለው አሰራር አሁን የተጀመረ እና በዚህም እናቶች ከወለዱ በሁዋላ የሚኖረውን መሞት በእጅጉ እንደቀነሰ መረዳት እንደሚቻልም ገልጸ ዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በእናቶች ጤንነት ዙሪያ አንዳንድ በጎ የሚባሉ ነገሮች መታየት መጀመራቸውንም አብራርተዋል፡፡
የእርግዝና ክትትል የመጀመሪያ ዙር 74 % ደርሶአል፡፡
በጤና ተቋማትና በሰለጠነ ባለሙያ ልጅን መውለድ 50% ደርሶአል፡፡
የእርግዝና ክትትል አራተኛው ዙር 43% ደርሶአል::
ከወሊድ በሁዋላ ክትትል 34 % ደርሶአል፡፡
ከላይ የተጠቀሰው መረጃ ተስፋ የሚሰጥና የሚያበረታታ ስለሆነ ለወደፊት የእናቶችንና ጨቅላ ህጻናቶቻቸውን ጤና በተሻለ መልኩ ለመጠበቅ የሚያስችለውን ርብርብ ማድረግ ከማህጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያዎች እና በዘርፉ ከተሰማሩት የጤና ባለሙያዎች ይጠበቃል ብለዋል አቶ ሸለመ ሁምኔሳ:: የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ባለሙያዎችን በምክር አገልግሎትና በስልጠና የማገዝና እና ብቃታቸውን ከፍ እንዲል የማድረግ ስራ ባለፈው አመት በ200 ሆስፒታሎች ላይ እንዲሰራ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዚህ አመት ደግሞ 100 ሆስፒታሎች ላይ እንዲሰራ እቅድ ተይዞ ድጋፍ ከሚያደርጉ አካላት ጋር የነደፈውን እቅድ እውን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ አብረውት ከሚሰሩት አካላት አንዱ ደግሞ ESOG የተሰኘው የኢትዮያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪ ሞች ማህበር ነው፡፡
ስለሆነም ላለፉት ሶስት ወራት የተካሄደው የMentor-ship ፕሮግራም የዚህ እቅድ አካል ሲሆን በዚህም የእናቶችና ጨቅላ ሕጻናቶቻቸው ጤንነት በተሻሻለ መንገድ እንደሚ ጠበቅ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል አቶ ሸለመ ሁምኔሳ፡፡
ከኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ እዮብ መሐመድ እን ደተናገሩት ፕሮጀክቱ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የተሰጠበት ምክንያ የእናቶችንና የጨቅላ ሕጻናቱን ጤንነት በማሻሻል ረገድ ከባለ ሙያዎቹ ጋር ማለትም በተለያዩ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች የሚሰራውን ስራ ማሻ ሻልን በሚመለከት ቅርብ የሆኑት የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር አባላት ስለሆኑ ፕሮጀ ክቱን እነሱ ቢያስተባብሩት ይሻላል በሚል እምት ነው፡፡ የዚህ ፕሮጀክት አተገባበር በተለያዩ መስተዳድሮች ባሉ የጤና ተቋማት የተለያየ እንደሚሆን አያጠራጥርም ብለዋል አቶ እዮብ መሐመድ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ፡፡
አንድ የማህጸንና ጽንስ ሐኪም ከሚሰራበት አጠቃላይ ሆስፒታል ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒ ታል እና ጤና ጣቢያ ወርዶ ከአንድ ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በመቆየት የማ ማከርና የህክምና አሰ ጣጥ አሰራሮችን ለመከታተል እንዲሁም የተለያዩ ልምዶችን ለማካፈል ጊዜውን መስዋእት ያደ ርጋል ተብሎ በማይጠበቅበት ሁኔታ ነገር ግን ሐኪሞቹ ለራሳቸው ቃልኪዳ ስለገቡና በእናቶችና ጨቅላዎቻቸው አለመጎዳት የሚረኩ በመሆኑ ድርጊቱን ተግባራዊ አድርገው ያሳዩባ ቸው አካባ ቢዎችን ተመልክተናል ብለዋል አቶ እዮብ፡፡ ለዚህም ከሚጠቀሱት መካከል በደብረብርሀን ሆስፒታል እና በአምቦ ሆስ ፒታል እንዲሁም በአሰላ ሆስፒታል የታየው የሙያ ተኞች መስዋእትነት ሳይገለጽ አይታለፍም እንደ አቶ እዮብ እምነት፡፡
አቶ እዮብ እንደገለጹት ከአሁን ቀደም የነበሩት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የጨቅላ ህጻናት ሞት ቁጥር በአሁኑ ወቅት የጨመረ ሲሆን የእናቶች ሞት ግን መቀነሱን መረጃዎች እየጠ ቁሙ ነው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የህጻናት ሞት ቁጥር ቀንሶ የነበረ ቢሆንም አሁን ያለው ሁኔታ ግን የተለየ ነው፡፡ የእናቶችና የጨቅላ ሕጻናቶችን ጤንነት ክህሎት ባላቸው ባለሙያ ዎች፤ አደረጃጀቱ በተሟላ ጤና ተቋም ካለምንም መዘግየት እንዲተገበር ለማድረግ የባለሙያዎ ችን እውቀትና ክህሎት በየጊዜው ከፍ እንዲል ማድረግ የሚያስችል ስራ ለመስራት የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ሞዴል ቀርጾ በስራ ላይ እንዲውል አድርጎአል፡፡
የእናቶች ሞት በአሁኑ ወቅት ቀንሶአል ቢባልም ምክንያቱን በተመለከተ ግን ምንም የተለወጠ ነገር የለም አቶ እዮብ እንደገለጹት፡፡ ባለፉት ሀያ አመታት በምክንያትነት የሚጠቀሱት የእና ቶች ሞት ምክንያቶች (በወሊድ ጊዜ የሚፈጠር ከፍተኛ የደም መፍሰስ፤ በእርግዝና ጊዜ የሚ ከሰት  የደም ግፊት፤ የተራዘመ ምጥ፤ ኢንፌክሽን…ወዘተ) ዛሬም ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ሲፈተሸ እውቀት እና ችሎታ አንሶ ሳይሆን ጥራት ያለው አሰራር ስለሌለ ነው የሚል ምስክርነት አግኝቶአል፡፡ ዛሬም እናቶ ችና ሕጻናቶቻቸው የሚሞ ቱበት ምክንያት የሚሰጣቸው የህክምና አገልግሎት ደካማ እና ጥራት የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህም ባለሙያዎችን አገልግሎት ከሚሰጡበት ጤና ተቋም ድረስ ሄዶ ልምድን ማካፈል እንዲሁም ስልጠናና የምክር አገልግሎት መስጠት የመያተኞችን ብቃት ስለሚያሳድግ ጥቅም የተገኘበት አሰራር መሆኑን ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፡፡


Read 5930 times