Wednesday, 02 October 2019 00:00

አፍሪካ በ2018 ብቻ በ67 ሚሊዮን አለማቀፍ ቱሪስቶች ተጎብኝታለች

Written by 
Rate this item
(0 votes)


የአፍሪካ አገራት በ2018 የፈረንጆች አመት ብቻ በ67 ሚሊዮን ያህል አለማቀፍ ቱሪስቶች መጎብኘታቸውንና አገራቱ በድምሩ 194.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘታቸውን ሰሞኑን የወጣ አንድ ሪፖርት አመልክቷል፡፡
ጁሚያ የተባለው ተቋም ሆስፒታሊቲ ሪፖርት አፍሪካ በሚል ርዕስ ያወጣው ሪፖርት እንደሚለው፣ በ2018 የአፍሪካ አገራትን የጎበኙ አለማቀፍ ቱሪስቶች ቁጥር በ2017 ከነበረው የ7 በመቶ እድገት ያሳየ ሲሆን፣ በአመቱ 11 ሚሊዮን ያህል አለማቀፍ ቱሪስቶች የጎበኙዋት ሞሮኮ ከአፍሪካ አገራት በርካታ ቁጥር ባላቸው ቱሪስቶች የተጎበኘች ቀዳሚዋ አገር ሆናለች፡፡
በአመቱ አፍሪካን ከጎበኙት አለማቀፍ ቱሪስቶች መካከል 71 በመቶ ያህሉ ለመዝናናት የመጡ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ለንግድና ለስራ ጉዳይ አፍሪካን የረገጡ ስለመሆናቸው ተነግሯል፡፡
የአህጉሪቱ የጉዞና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ በአመቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለ24.3 ሚሊዮን አፍሪካውያን የስራ ዕድል መፍጠሩን የገለጸው ሪፖርቱ፣ ዘርፉ በአህጉሪቱ ከተፈጠረው አጠቃላይ የስራ ዕድል 6.7 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝም አመልክቷል፡፡


Read 2146 times