Print this page
Monday, 09 September 2019 12:23

ዳሸን ባንክ በሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስም ቅርንጫፍ ከፈተ

Written by  መንግሥቱ አበበ
Rate this item
(4 votes)

 ዳሸን ባንክ አ.ማ አዲስ ባስገነባው ዘመናዊ የዋና መ/ቤት ሕንፃ ላይ በዓይነቱና በአገልግሎቱ ልዩ የሆነ ቅርንጫፍ መክፈቱን አስታወቀ፡፡
ከትናንት በስቲያ በታዋቂው ኢትዮጵያ ባለሀብት በሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስም የተሰየመውንና በዋና መ/ቤቱ ሕንፃ ውስጥ የተከፈተውን ቅርንጫፍ በክብር እንግድነት ተገኝተው መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር ታከለ ኡማ ናቸው፡፡  ቅርንጫፉ ደንበኛ ተኮር ሆኖ የተዋቀረ ሲሆን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለዕድሜ ባለፀጐች፣ ለውጭ አገር ኢንቨስተሮች፣ ከወለድ ነፃ አገልግሎት፣ ለኮርፖሬት አገልግሎት፣ ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና ለሌሎችም አገልግሎቶች የተዘጋጁ ዴስኮች እንዳሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዳሸን ባንክ በዚሁ የቅርንጫፍ መ/ቤት ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ 718 ሺህ ብር፣ ለእናት ወግ በጐ አድራጐት ድርጅት 296 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
መስከረም 1995 ዓ.ም የተመሠረተው ዳሸን ባንክ በአሁኑ ወቅት በመላ አገሪቱ 415 ቅርንጫፎች እንዳሉት ይታወቃል፡፡  

Read 2910 times